የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጅማ ሪጅን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሠራተኞች ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰፋት ይፈልጋል፡፡
የጅማ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር EEU/SC&PGS/JB/NCB-003/2018
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጅማ ሪጅን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሠራተኞች ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰፋት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የዕቃው ዓይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
የጨረታ ማስከበሪያ(CPO) |
የጨረታው መዝጊያ ቀን |
የጨታው መክፈቻ ቀን |
|
1 |
ጃኬት እና ሱሪ |
በቁጥር |
629 |
22,000.00 |
ጥር 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 |
ጥር 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 |
|
2 |
ጋዎን |
በቁጥር |
32 |
|||
|
3 |
ኮት እና ሱሪ ከነ ገበሩ |
በቁጥር |
76 |
|||
|
4 |
ቱታ |
በቁጥር |
25 |
1. ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑን ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
2. ተጫራቾች የመንግስት ድርጅቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ እንዲችሉ በግዥ ኤጀንሲ ዌብሳይት ላይ የተመዘገቡ መሆኑን ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው::
3. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 6 በመምጣት የማይመለስ ብር 300.00 በመከፈል መግዛት ይችላሉ፡፡ ስለሆነም በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ አካውንት ቁጥር EEU Jimma Region 1000156094157 ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን ስሊፕ በመያዝ በጂማ ሪጅን ፋይናንስ ቢሮ ቀርበው ደረሰኝ እንዲቆርጡ እናሳስባለን፡፡
4. አድራሻ - በጅማ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ሕከምና እና ግብርና ኮሌጅ አጠገብ በሚገኘው በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በጅማ ሪጅን ሰፕላይ ቼን እና ንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 6
5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውንና የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት በባንከ በተረጋገጠ ቼክ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና (Bid Bond) 22,000.00 (ሀያ ሁለት ሺ) በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥር 14 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ከላይ በተገለፀ አድራሻ ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ቴከኒካል «ኦሪጅናል እና ኮፒ” ፋይናንሻል «ኦሪጅናል እና ኮፒ » ባንከ ጋራንቲ ‹‹ኦሪጅናል እና ኮፒ » በማለት በተለያየ ፖስታ በማሸግ እና ሁለቱን በአንድ ትልቅ ፖስታ በማድረግ ጨረታ ቁጥር EEU/SC&PGS/JR/NCB-002/2018 የሚል ምልከት በማድረግ እስከ ጥር 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 6 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
7. ጨረታው ከላይ በተጠቀሱት ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተገለፀው አድራሻ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
8. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 047-2113757 መደወል ይችላሉ፡፡
9. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጅማ ሪጅን
