በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጐንደር መንገድ ጥገና ዲስትሪከት ለአዘዞ-ጐንደር መንገድ ፕሮጀከት አገልግሎት የሚሆን ብዛቱ ከ4,000 እስከ 10,000 ኩንታል የሚደርስ ሲሚንቶ ከናሽናል ሲሚንቶ ለሚ ፕላንት ወደ ጐንደር ከተማ በጨረታ አወዳድሮ ማጓጓዝ ይፈልጋል።
ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የትራንስፖርት አገልግሎት ግዢ ጨረታ ቁጥር GN-007/2018
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጐንደር መንገድ ጥገና ዲስትሪከት ለአዘዞ-ጐንደር መንገድ ፕሮጀከት አገልግሎት የሚሆን ብዛቱ ከ4,000 እስከ 10,000 ኩንታል የሚደርስ ሲሚንቶ ከናሽናል ሲሚንቶ ለሚ ፕላንት ወደ ጐንደር ከተማ በጨረታ አወዳድሮ ማጓጓዝ ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታከስ ከሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ እና የንግድ ምዝገባ ፈቃዳቸው በቂ የጭነት ትራንስፖርት አቅም ያላቸው ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ (የመልካም ሥራ አፈፃፀም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ) ድርጅቶች ለዚህ ጨረታ ሲባል የተዘጋጀውን ሰነድ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር እቃ ግዥ ቡድን 1 እና ቡድን 2 ቢሮ ወይንም ጐንደር ከሚገኘው የዲስትሪክቱ ጽ/ቤት በነፃ መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት 15 ተከታታይ ቀናት ከፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን ከ15ኛው ቀን ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር እቃ ግዥ ዳይሬከቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡
መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 0911-664988/0991183657 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጐንደር መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
