የሸኖ ከተማ ገንዘብ ጽህፈት ቤት በ2018 በጀት ዓመት በሸኖ ከተማ ውስጥ ለሚሠራው የጠጠር የውስጥ ለውስጥ መንገድ የሚውል የተለያዩ ንብረቶችን በጨረታ አወዳድሮ በኪራይ ለማሠራት ይፈልጋል
በኦሮሚያ ክልል የሸኖ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
ለሁለተኛ ጊዜ የጨረታ ማስታወቂያ
የሸኖ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በሸኖ ከተማ ውስጥ ለሚሠራው የጠጠር የውስጥ ለውስጥ መንገድ የሚውል፦
- Chain excavator 172Hp and above
- Chain excavator 172Hp and above with Jack Hammer
- Roller 16ton and above
- Shower tracker 16,000Lt and above
- Dump truck rent minimum of 16M3: በጨረታ አወዳድሮ በኪራይ ለማሠራት ይፈልጋል።
ስለዚህ በሥራ ዘርፉ የዘመኑን ግብር የከፈላችሁ፤ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላችሁ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT 15% ተመዝጋቢ የሆናችሁ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN ያላችሁ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሸኖ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በግንባር በመቅረብ ዝርዝር መጠይቆችን የያዘውን ሰነድ በማይመለስ በብር 1000 (አንድ ሺህ) በካሽ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በዝርዝር የተመለከተውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በካሽ ወይም ሲፒኦ “CPO “ማስያዝ አለባቸው።
- ይህ ጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ22ኛው ቀን በ8፡00 ታሽጎ ከቀኑ 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ተወካዮች በተገኙበት ይከፈታል፣ ይህ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
ማሳሰቢያ ፡-
- ጨረታውን ያሸነፈ ድርጅት ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ውሉን ፈጽሞ ሥራውን የመጀመር ግዴታ አለበት።
- ተጨማሪ መግለጫዎች ተዘጋጅቶ በሚሸጠው በጨረታ ሰነዱና specification ላይ በዝርዝር ይገኛል።
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ /አማራጭ/ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ: - ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ በሚወስደው መንገድ 78 ኪሎ ሜትር ሸኖ ከተማ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስቁ: - 0910 093 362 በመደወል ጠይቆ መረዳት ይቻላል።
በኦሮሚያ ክልል የሸኖ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
