Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የመቐለ ሪጅን ጽ/ቤት
  • Address በመቐለ ከተማ ፕላኔት ሆቴል ወረድ ብሎ የሚገኝ ዛምራ ህንፃ ላይ የመቐለ ሪጅን ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ሳፕላይ ቼይን ንብረትና ጠ/አ ቢሮ ቁጥር 304፡ ትግራይ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251342406712
  • Website
  • Deadline09 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Securityለሚጫረቱበት ተሽከርካሪ ለእያንዳንዱ የጨረታ መነሻ ዋጋ 20 በመቶ (20%)
  • opening date2026-01-09 00:00:00
  • Categories Vehicle , Used Items

የኢትዮጵያ ኤሌከትሪክ አገልግሎት መቐለ ሪጅን ንብረት የሆኑት የተለያዩ ቀላልና መካከለኛ ያገለገሉ 3 ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የመቐለ ሪጅን ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር መቐ/ሪ/ን/ማ/05/2018 -ሎት-5

 

የኢትዮጵያ ኤሌከትሪክ አገልግሎት መቐለ ሪጅን ንብረት የሆኑት የተለያዩ ቀላልና መካከለኛ ያገለገሉ 3 ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከፕላኔት ሆቴል ወረድ ብሎ የሚገኝ የዛምራ ኮንስትራክሽን ህንፃ ላይ የመቐለ ሪጅን ፅ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 302 ቀርበው የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ዝርዝር የተሽከርካሪዎች መረጃ የያዘ የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ገዝተው ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት፤ ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት እስከ 11፡0o ሰዓት ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ተሽከርካሪዎችን በመቐለ ከተማ 05 ቀበሌ ደንበስኮ ፊት ለፊት የሚገኝ የመቐለ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዕቃ ግምጃ ቤት ቅጥር ግቢ በመሄድ መመልከት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ተሽከርካሪ ለእያንዳንዱ የጨረታ መነሻ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Bond) በመቐለ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት™ (MEKELLE REGION ELECTRIC UTILITY) ስም ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ የጨረታ ቁጥሩን በመግለፅ ጥር 01 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ብቻ በመቐለ ከተማ ከፕላኔት ሆቴል ወረድ ብሎ የሚገኝ ዛምራ ኮንስትራክሽን ህንፃ 3ኛ ፎቅ የመቐለ ሪጅን ሳፕላይ ቼይን ንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 304 በመምጣት ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ጨረታው ጥር 01/2018 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት ከላይ በተገለፀው አድራሻ ይከፈታል።
  5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ 15% ተጨማሪ እሴት ታከስን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
  6. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0342406712 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  7. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

የመቐለ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት

 

Save Tender