በኦለንጭቲ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በ2018 ዓ.ም በመደበኛ በጀት ኦርጅናል የፅዳት እቃዎች፣ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ የብረት ቧንቧ እና መገጣጠሚያ እና HDPE Pipe እና መገጣጠሚያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በኦለንጭቲ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦለንጭቲ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በ2018 ዓ.ም በመደበኛ በጀት ኦርጅናል የፅዳት እቃዎች፣ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ የብረት ቧንቧ እና መገጣጠሚያ እና HDPE Pipe እና መገጣጠሚያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም እጩ ተጫራቾች ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉና ንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሠነድ ከነዋጋ ማቅረቢያው በታሸገ ኤንቨሎፕ ኮፒና ኦርጅናል በመለየት ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታውም በ16ኛው ቀን ከቀኑ 6፡30 ታሽጎ በዕለቱ በ8፡00 እጩ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸው ባሉበት በኦለንጪቲ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ቢሮ ቁጥር 3 ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000.00 በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም እጩ ተጫራች ያሸነፈበትን ዕቃ ለማቅረብ አስቀድሞ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ለመፈረም ፈቃደኛ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች በፌዴራል ወይም በኦሮሚያ የገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ የአቅራቢዎች መዝገብ ላይ የተመዘገቡ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 500.00 ለእያንዳዱ ሠነድ በመክፈል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአለንጭቲ ከተማ መጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ቁጥር 3 መግዛት ይችላሉ፡፡
- እጩ ተጫራቾች የተጨማሪ ታክስ ከፋይ ወይም ቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- እያንዳንዱ እጩ ተጫራች የንግድ መለያ ቁጥር (TIN number) ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ካሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን ካሸነፈ ከመ/ቤቱ ጋር ውሉን ከፈረመ በኋላ ዕቃውን ለኦለንጭቲ ከተማ መጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት በራሱ ማጓጓዣ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
- የጠቅላላ የግዥ ዋጋ ብር 20,000 ከሆነ 3% ዊዞልድንግ ታክስ (withholding tax) እና ከ20,000 በላይ ከሆነ 7.5% ታክስ ተቀናሽ ይሆናል፡
- ከቀረበው አጠቃላይ የግዢ ዋጋ መስሪያ ቤቱ 20% እና ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ ሙበት የተጠበቀ ይሆናል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0221131046/0221130076
በኦለንጭቲ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
