የመንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት በአማራ ክልል በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የሚገኝ መንግስታዊ የሆነ የልማት ድርጅት ሲሆን ድርጅቱ እያስገባቸው ላሉ ለደ/ማርቆስ ከተማ አልማ G+10 ሆንጻ ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል የኤሌክትሮ መካኒክ አቅርቦትና ገጠማ፣ የኮርኒስ አቅርቦትና ስራ፣ የስካይ ላይት አቅርቦትና ስራ እና ለደ/ብርሃን ጠቅላላ ሆስፒታል አልሙኒየም ሃንድ ሬል አቅርቦት እና ስራ ከዚህ በታች በተቀመጠው ዝርዝር መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
Menkorer Construction Enterprize (የመንቆረር ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ)
በድጋሜ የወጣ ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር መኮ/ግ/569/ጨ-01
የመንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት በአማራ ክልል በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የሚገኝ መንግስታዊ የሆነ የልማት ድርጅት ሲሆን ድርጅቱ እያስገባቸው ላሉ ለደ/ማርቆስ ከተማ አልማ G+10 ሆንጻ ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል የኤሌክትሮ መካኒክ አቅርቦትና ገጠማ፣ የኮርኒስ አቅርቦትና ስራ፣ የስካይ ላይት አቅርቦትና ስራ እና ለደ/ብርሃን ጠቅላላ ሆስፒታል አልሙኒየም ሃንድ ሬል አቅርቦት እና ስራ ከዚህ በታች በተቀመጠው ዝርዝር መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
- ምድብ 1 ለደ/ማርቆስ ከተማ አልማ G-10 የኤሌክትሮ መካኒክ አቅርቦትና ገጠማ
- ምድብ 2 ለደ/ማርቆስ ከተማ አልማ G-10 የኮርኔስ አቅርቦትና ስራ
- ምድብ 3 ለደ/ማርቆስ ከተማ አልማ G+10 የስካይ ላይት አቅርቦትና ስራ
- ምድብ 4 ለደ/ብርሃን ጠቅላላ ሆስፒታል አልሙኒየም ሃንድ ሬል አቅርቦት እና ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት፡-
- ተጫራቾች የምትጫረቱበትን ሰነድ ያንዱን ዋጋ በጥንታቄ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 /አስራ አምስት ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 13 ማስገባት አለባችሁ።
- ጨረታው የጨረታ ማስገቢያው በተጠናቀቀ በቀጣይ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ 3፡30 ላይ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በበአላት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡ ሆኖም በራሳቸው ፈቃድ በመክፈቻው ቀን ባይገኙ የጨረታውን መክፈት አያግደውም፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የተመዘገበና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የነጋዴነት መለያ ቁጥር፣ የዘመኑን ግብርየገበሩና የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ደ/ማርቆስ ከተማ በሚገኘው መንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ቁጥር 11 ድረስ በመቅረብ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- በየምድባቸው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ኮፒ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው።
- በምድብ 1 ላይ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የቴክኒካል እና ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው።
- በምድብ 1 ላይ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የመልካም ስራ አፈጻጸም አንድ እና ከዚያ በላይ የሰሩበትን ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠ/ዋጋ 2% በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ 10% በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና፣ የመድን ዋስትና ወይም በሲፒኦ ማስያዝ አለበት፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፋቸውን እቃዎች በየምድቡ የተዘረዘሩትን በራሱ ትራንስፖርት በየፕሮጀክቱ በማቅረብ ሰርቶ ማስረከብ አለበት፤
- አሸናፊው ድርጅት በምድብ 1፣ በምድብ 3 እና ምድብ 4 ላይ ያሉትን በተያያዘው ድሮይንግ መሰረት ሰርቶ ማስረከብ አለበት፡፡
- የእሸናፊው ድርጅት አቅርቦትና ስራ በባለሙያ ተረጋግጦ ማለፍ አለበት፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በየምድባቸው በሎት ወይም በጥቅል ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀላቸው ባሉት 7 /ሰባት የስራ ቀናት ውስጥ ውል በመያዝ አስፈላጊ ማቴሪያሎችን በማቅረብ ስራውን መጀመር አለባቸው።
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ወይም አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0920514407 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በደ/ማርቆስ ከተማ/አስተዳደር የመንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት
