የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ፣ የቤት ማስዋቢያ፣ አልባሳት፣ ጫማ፣ የቤት ዕቃ፣ እስፔርፓርት፣ ምግብ ነክ፣ ኮንስትራክሽን፣ የፅዳት ዕቃ እና ልዩ ልዩ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ፣ የቤት ማስዋቢያ፣ አልባሳት፣ ጫማ፣ የቤት ዕቃ፣ እስፔርፓርት፣ ምግብ ነክ፣ ኮንስትራክሽን፣ የፅዳት ዕቃ እና ልዩ ልዩ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን እቃዎች 17/04/2018 ጀምሮ ሳምፕል በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገለፃል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
- በዘርፉ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብርሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣ እንዲሁም የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ
- ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ እቃዎቹን ለመግዛት የሚቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ማቅረብ የሚችል፡፡
- ግልጽ ጨረታ ቅ/ጽ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ በመሙላት በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ተጫራቹ በጨረታው አሸንፎ የገዛውን እቃዎች ክፍያውን በ05 ቀናት ውስጥ መፈፀም አለበት፡፡
- እቃዎቹን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
- በጨረታው ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
- አሳማኝ የሆነ ምክንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች እቃዎቹን ካሸነፈ በኋላ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈልግ እንደየቦታው ርቀት በቀነ ገደብ መሸኛ ሲሰጣቸው ይችላል፡፡
- ተጫራቹ ዕቃዎችን አሽንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም።
- ተጫራቾች የሞሉትን የግልፅ ጨረታ ሰነድ ከ17/04/2018 ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በጅግጅጋ ጉ/ኮ/ቅ/ጽ/ቤት የዕቃ አወጋገድ ቢሮ በመቅረብ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን፣ ጨረታው በ20/04/2017 3:45 ተዘግቶ ከረፋዱ 4:00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
NB:- አሸናፊ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) 15% (አስራ አምስት ፐርሰንት) የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ፤ ሳምፕል ሳያዩ የሚጫረቱ ተጫራቾች ቅ/ጽ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም።
የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት
