Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ የይገም ጤና አጠባበቅ ጣቢያ አገልግሎት የሚውሉ፡-ሎት 1፡-የፅህፈት መሳርያዎችሎት2፦የተለያዩ ህትመቶችሎት3፡ የፅዳት እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ማሳተም ይፈልጋል።በዚህ

በአማራ ብሄራዊ ከልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ የይገም ጤና አጠባበቅ ጣቢያ


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ የይገም ጤና አጠባበቅ ጣቢያ አገልግሎት የሚውሉ፡-ሎት 1፡-የፅህፈት መሳርያዎችሎት2፦የተለያዩ ህትመቶችሎት3፡ የፅዳት እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ማሳተም ይፈልጋል።በዚህ መሰረት፡-

  1. በዘርፉ የተሰማራና የዘመኑን ግብር የከፈለበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር ያላቸው።
  3. የገዥው መጠን ከብር 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 3 የተጠቀሱትና ሌሎች የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  5. የሚገዙ እቃዎችን እና የሚታተሙት ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ለእያንዳንዱ ሎት ማስያዝ አለባቸው።
  7. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውንና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው።
  8. በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም።
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ፖስታዎች ማለትም አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በይገም ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታውን ሰነድ ገቢ ማድረግ ይችላሉ።
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ጨረታው በተዘጋበት ቀን ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ላይ በመንዝ ማማ ምድር ወረዳ በይገም ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 1 ውስጥ በይፋ ይከፈታል። ባይገኙም ከመከፈት አይታገድም።
  11. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል።
  12. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 50/ ሃምሳ ብር ብቻ/ በመክፈል ከመንዝ ማማ ምድር ወረዳ በይገም ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 1 መግዛት ይችላሉ።
  13. ተጫራቾች ያሸነፉትን ንብረት በራሳቸው ወጭ ወደ ጤና ተቋሙ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው።
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09 11-09 41-51/ 09 20 33 20 76 ደውለው ይጠይቁ።

 

በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ማማ ምድር ወረዳየይገም ጤና አጠባበቅ ጣቢያ

Save Tender