Tender Detail

Tender Details

  • Company የደብረ ብርሃን ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
  • Address , Phone: 0116377277
  • Website
  • Deadline11 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2026-01-11 00:00:00
  • Categories Generators , Laboratory Equipment And Chemicals , Camera

የደ/ብርሃን ከተማ ውሃና ፍሳሽ ድርጅት ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የመበየጃ ማሽን፣ ሎት 2 ጀኔሬተር፣ ሎት 3 የላብራቶሪ እቃ፣ ሎት 4 ፎቶ ካሜራ በዘርፉ ከተሰማሩ ንግድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 0014/2018

 

የደ/ብርሃን ከተማ ውሃና ፍሳሽ ድርጅት ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የመበየጃ ማሽን፣ ሎት 2 ጀኔሬተር፣ ሎት 3 የላብራቶሪ እቃ፣ ሎት 4 ፎቶ ካሜራ በዘርፉ ከተሰማሩ ንግድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር ለሚፈልጉ፤፤

  1. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቲን ነምበር ሰርተፊኬት ያለው የግዥ የቫት ተመዝጋቢ የሆነና የዘመኑን ግብር ማስረጃ ለመክፈላቸው አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን ሰነድ ኦርጅናሉንና ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ፖስታ የአንዱ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በትክክል በመሙላት ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣ የድምር ስህተት ካለ በአንድ መስመር በመሰረዝ ፓራፍ በማድረግ የተስተካከለውን በምርመራ ዓምድ ላይ በትክክል መሙላት ይጠበቅባቸዋል፣
  3. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ እና ቅዳሜ እስከ 500 በሥራ ሰዓት የተዘጋጀው ሰነድ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በደ///////ቤት ቢሮ /2 በመቅረብ መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፣
  4. ተጫራቾች ቴክኒክ ሰነድ ለሚያስፈልጋቸው ሌሎች 1,2,3,4 ለብቻው ቴክኒካል ሰነድ በማዘጋጀትና ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት በሁለት በተለያዩ በታሸገ ፖስታ በማሸግ ለዚሁ ወደ ተዘጋጀው ቴክኒካል ሰነድ ጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ በተገለፀው ጊዜ ገደብ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ 16ኛው ቀን ድረስ 329 ሰዓት ክፍት ሆኖ በዚሁ ቀን 330 ይታሸጋል፣ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 400 ሰዓት የደ/ /////ድርጅት በአዳራሽ ውስጥ ይከፈታል የመክፈቻው ቀን በዓል ላይ ከዋለ በማግስቱ ይከፈታል፡፡
  6. የጨረታውን ማስከበሪያ ተጫራቾች የተጫረቱበትን የጠቅላላ ዋጋ 1% በማስላት በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል ሆኖም በጥሬ ገንዘብ የሚያስይዝ ተጫራች ያስያዘበትን የገንዘብ መቀበያ ሰነድ ኮፒ በማድረግ በጨረታ ሰነዱ አሽጎ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፣
  7. አሸናፊው የሚለየው በነጠላ ዝቅተኛውን በማወዳደር ሆኖ የተሞላው ዋጋ ከወቅቱ ገበያ ጥናት በላይ ከሆነ ውድቅ ይደረጋል፣
  8. አሸናፊው ድርጅት ወዲያውኑ ውል ይፈጽማል የውል ማስከበሪያ በአሸነፈበት የጠቅላላ ዋጋ ብር 10% ያሲዛል፣
  9. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ማሻሻያ ማድረግ ወይም እራሳቸውን ከጨረታው ማግለል አይችሉም፣
  10. ተወዳዳሪዎች ራሳቸውን ከጨረታው ማግለል ቢፈልጉ ጨረታው ከመታሸጉ በፊት ማመልከቻ በመፃፍና ሳጥን ውስጥ በማስገባት ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል ይችላሉ፣
  11. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈበትን እቃ በራሱ ወጪ ////አገ//ቤት ቢሮ ማድረስ ይጠበቅበታል፣
  12. አሸናፊው ድርጅት /ቤቱ በጠየቀው እስፔስፊኬሽን መሠረት እቃውን ማቅረብ ይኖርበታል፣
  13. ድርጅቱ እንደ አስፈላጊነቱ ጨረታውን 25% በመጨመርና በመቀነስ ማሻሻል ይችላል፣
  14. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን የተለያዩ እቃዎች በድርጅቱ ባለሙያ ጥራቱ ተገምግሞ ትክክል ሆኖ ሲረጋገጥ ክፍያ የሚከፈል ይሆናል፣
  15. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. የጨረታ ሰነድ ወይም የጨረታ ዋጋ ፀንቶ እሚቆይበት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን አንስቶ 45 ቀናት የፀና ይሆናል
  17. አንዱ በሌላው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፤
  18. ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011-637-72-77 መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የደብረ ብርሃን ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

Save Tender