የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የደቡብ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለቅ/ፅ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል የጽህፈት ቤቱ ሰራተኞች ጠዋት እና ማታ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት እና የሙሉ ቀን ሥራ ትራንስፖርት አገልግሎት ሥራ መግዛት ይፈልጋል
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የደቡብ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ደቡብ ቅ/ጽ/ቤት/003/2018
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የደቡብ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለቅ/ፅ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል
|
ሎት
|
የእቃው/የአገልገሎቱ አይነት
|
ማብራሪያ
|
|
ሎት 1
|
የጽ/ቤቱ ሰራተኞች ጠዋት እና ማታ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት
|
|
|
ሎት 2
|
የጽ/ቤቱ የሙሉ ቀን ሥራ ትራንስፖርት አገልግሎት
|
|
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶች መግዛት ይፈልጋል። በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን። በዚህም መሰረት የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ የታደሰ ሊብሬ እና የሶስተኛ ወገን የመድን ዋስትና/ኢንሹራንስ ማሟላት እና ማቅረብ የሚችሉ። ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለሎት1፡- 5000 (አምስት ሺህ ብር) ለሎት፡-2 5000 (አምስት ሺህ ብር) በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ደቡብ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሚል በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ከቴክኒካል ሰነድ ጋር ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ በጋዜጣ « ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ሲሆን ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ድረስ ለተከታታይ 10 (አስር) የሥራ ቀናት ቅ/ጽ/ቤቱ ከክፍያና ፋይናንስ ቡድን በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ማስገባት ይኖርባችዋል።
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በእለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ክፍል ይከፈታል።
- ተጫራቾች ጨረታው (ቴክኒካል ሰነድ) በሚከፈትበት ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ተሽካርካሪዎቹን ቅ/ጽ/ቤቱ ድረስ በአካል በመቅረብ የቴክኒክ ፍተሻ ማድረግ የሚጠበቅባችሁ ሲሆን በቴክኒካል ያላለፈ ተሽከርካሪ ለዋጋ ውድድር አይቀርብም።
- ተጫራቾች ለሚሰጡት አገልግሎት ነዳጅ፣ ቅባት እና ማንኛውም ወጪ በራሱ የሚሸፍን ይሆናል።
- የጨረታውን ሙሉ ዝርዝር መረጃ በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ።
- የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ ከተዘጋ በኋላ የሚደርስ ማንኛውም ሰነድ ሳይከፈት ለተጫራቹ ይመለስለታል።
- ተጫራቾች የሚጫራቱበትን እቃ አገልግሎት የአንዱን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት በመለየት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) የሥራ ቀናት ቅ/ጽ/ቤቱ በመቅረብ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፦ ከኃይሌ ጋርመንት ወደ ሰፈራ በሚያስኬደው መንገድ ወረድ ብሎ ህዩንዳይ ፊት ለፊት በሚገኘው ሃና ፉሪ ግንባታ ሳይት ውስጥ
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09-66-42-62-98 መጠየቅ ይችላሉ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የደቡብ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት
