የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴንሽን ኤም.ኤን.ኤስ ማኑፋክቸሪንግ እና ትሬዲንግ ለውጪ አገር እና ለአገር ውስጥ የተዘጋጁ ከ300 ቶን በላይ የተለያዩ የፎጣ አይነቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን
የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴንሽን ኤም.ኤን.ኤስ ማኑፋክቸሪንግ እና ትሬዲንግ ለውጪ አገር እና ለአገር ውስጥ የተዘጋጁ ከ300 ቶን በላይ የተለያዩ የፎጣ አይነቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ አሸናፊው ድርጅት በውል በተደገፈ እስከ 2 ዓመት የጊዜ ገደብ የድርጅቱን የፎጣ ምርት ዋጋ አከፋፋይ ሆኖ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
በዚህም መሠረት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሠነድ ገዝቶ መወዳደር ይችላል፡፡
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ሰነዶች፡-
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በጠቅላላ 1% ሲፒአ ማስያዝ የሚችሉ፣
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የዘመኑን ግብር የከፈለበትን መስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለገጣፎ ለገዳዲ ከሚገኘው ድርጅታችን ቢሮ ቀርበው የማይመለስ 500 (አምስት መቶ) ብር በመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ኤም.ኤን.ኤስ ማኑፋክቸሪንግ እና ትሬዲንግ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት 1000717629101 በማስገባት ሰነዱን ከገበያ እና ሽያጭ ቢሮ መግዛት የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ለገጣፎ ለገዳዲ በሚገኘው በድርጅቱ ቅጥር ግቢ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን በ8፡00 ተዘግቶ በ8፡10 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- 8ተኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ-
- አሸናፊው ድርጅት የተጠቀሰውን ጠቅላላ የፎጣውን መጠን የሚያነሳ ከሆነ የ25% የዋጋ ቅናሽ ከአከፋፋይ ተጠቃሚ ይሆናል፤
- አሸናፊው ድርጅት ከአጠቃላይ መጠኑ ከ75% በላይ የሚያነሱ ከሆነ የ20% የዋጋ ቅናሽ ተጠቃሚ ይሆናሉ።
- ከ50% በላይ የሚያነሱ ከሆነ ደግሞ ከዋናው የጅምላ አከፋፋይ 15% የዋጋ ቅናሽ የሚደረግላቸው መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡
- 30% መጠን የሚያነሱ ከሆነ ደግሞ ከዋናው የጅምላ አከፋፋይ ዋጋ የ10% የዋጋ ቅናሽ ተጠቃሚ ይሆናሉ፤ ፋውንዴሽን
- አሁን ያለው የአከፋፋይ የመሽጫ ዋጋ 900 ብር ሲሆን ቫትን እና ኤክሳይስ ታክስ ይጨምራል።
ለበለጠ መረጃ ስ.ቁ:- 0912736548፣ 0911412626፣ 0914763609፣ 0116679035/59
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን
