Tender Detail

Tender Details


ድርጅታችን ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ (ኢኢግ) በስሩ በሚያስተዳድራቸው ኢንዱስትሪዎችና ዋና መ/ቤት በንብረት ክፍል ተከማችተው የሚገኙ የምርት ግብዓትን ጨምሮ የተለያዩ ነገሮችን በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ ባሉበት ሁኔታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Ethio Engineering Group (ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር: ኢኢግ/ንአአኮ/ብግጨ/04/2018

 

ድርጅታችን ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ (ኢኢግ) በስሩ በሚያስተዳድራቸው ኢንዱስትሪዎችና ዋና መ/ቤት በንብረት ክፍል ተከማችተው የሚገኙ የምርት ግብዓትን ጨምሮ የተለያዩ የመበየጃ ኤሌክትሮዶች፣ የተለያዩ የግንባታ ዕቃዎች፣ የተለያዩ ጉልበት ያላቸው የእርሻ ትራክተሮች፣ የተለያዩ (HYUNDAI, XCMG, SHANTU, Liebherr) ማሽነሪዎች መለዋወጫ፣ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች፣ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች፣ የተለያዩ የመበየጃ ማሽኖች፣ የመቁረጫ ማሽኖች፣ የተለያዩ ያገለገለ ማምረቻ ማሽኖች፣ የተለያዩ የዩትሊቲ ዕቃዎች፣ የእጅ ማሽኖች እና ኮንስትራክሽንና የቧንቧ መለዋወጫ፣ የተለያዩ አነስተኛና ከባድ ተሽከርካሪ መኪናዎች መለዋወጫ፣ የተለያዩ የትራክተር ተቀፅላ መሳሪያዎች (Implemnt spare) መለዋወጫ ዕቃዎች፣ የተለያዩ ያገለገሉ ጀነሬተሮች፣ የተለያዩ የውሃ መርጫ (Try pole) እና PFC (power facter)፣ የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎችና መሳሪያዎች፣ የተለያዩ ያገለገለ አሮጌ ጎማዎች፣ የተለያዩ ኬሚካሎች፣ የተለያዩ የፕሮጀክት እቃዎች እና የተለያዩ የማሽን አካላት (scrap) በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ ባሉበት ሁኔታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ማናቸውም ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለው ወይም በኢትዮጵያ ህግ መሰረት የተቋቋመ የንግድ ደርጅት መጫረት ይችላል፣
  2. በኢትዮጵያ ህግ መሰረት የተቋቋመ የንግድ ደርጅት ተጫራች ከሆነ ህጋዊነቱን የሚያሳዩ ሰነዶች (የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የታክስ ምዝገባ እና የታክስ ከፋይነት ሰርተፍኬት) ማቅረብ ይጠበቅበታል፣
  3. ኬሚካል ላይ የሚሳተፉ ተጫራቾች ለምን አገልግሎት እንደሚያውሉት ማረጋገጫ በፅሁፍ የሚያቀርቡና ኃላፊነት የሚወስዱ መሆን አለባቸው፣
  4. ዕሴት በመጨመር መልሶ ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ በሽያጭ ለሚወገዱ ንብረቶች ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ መሆናቸውን ማርጋገጫ ማቅርብ ይኖርበታል፣
  5. ለጨረታ የሚያስፈልጉ ቅፆችን አዲስ አበባ ሜክሲኮ አደባባይ ከፈዴራል ፖሊስ ዋና መ/ቤት ወደ ሳር ቤት በሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ዝቅ ብሎ በሚገኘው የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፑ ዋና መስሪያ ቤት Block-B 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር-203 የንብረት አስወጋጅ አብይ ኮሚቴ ቢሮ በመቅረብ የዕቃዎቹንና የንብረቶቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ከዚህ በታች አንቀጽ 4 በተመለከተው መሰረት የማይመለስ ብር 1000.00 በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የተጠቀሱትን ሰነዶች በመግዛት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹን ከሰነዱ ላይ በተጠቀሱት ቦታዎች በመሄድ መመልከት ይችላሉ፣
  7. ንብረቶቹን ካሉበት የግሩፑ ቦታ እስከ መዳረሻ ያለ የትራንስፖርት ወጪ /ለማጓጓዣ/፣ ለጫኝና አውራጅ፣ የመቆራረጫ፣ ለማስመዘን፣ ንብረቱን ካለበት ቦታ ለማንቀሳቀስ የሚወጣ ወጪ እና ሌሎች ተያያዥ ወጪዎች በገዥው ይሸፈናል፣
  8. የሚወገዱ ንብረቶች ጋር ተያይዞ ያልተከፈለ የንብረት ወይም የተሽከርካሪ የስም ማዘዋወሪያና ቦሎ ክፍያ ወጪ እንዲሁም ያልተከፈለ ዕዳ ካለበት በተጫራቾች የሚሸፈን ይሆናል፣
  9. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት ከሎት 01 እስከ ሎት 19 ድረስ ለተጠቀሱት ዕቃዎች ተጫራቹ የሚወደጉ ንብረቶችን ግምታዊ ዋጋ መሰረት በማድረግ 2 በመቶ (2%) እንዲሁም ለተሽከርካሪ፣ ትራክተርና ለኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች አምስት በመቶ (5%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፑ ዋና መስሪያ ቤት Block-B የንብረት አስወጋጅ አብይ ኮሚቴ ቢሮ ቁጥር-203 በሚገኝ ሳጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
  10. ጨረታ የመገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) ያላቀረበ እና የማያሻማና ግልፅ ያልሆነ እንዲሁም ለማጭበርበር ተግባር የቀረበ የዋጋ ማቅረቢያን በመለየት ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፣
  11. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን ጠዋት 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሜከሲኮ በሚገኘው የኢ.ኢ.ግ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ የዕረፍት ወይም በዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡ እንዲሁም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፣
  12. በጨረታ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ7 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለግሩፑ ገቢ ይደረጋል፣
  13. ግሩፑ ባወጣው ጨረታ ሰነድ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድሩ ውድቅ ይሆናል፣
  14. አሸናፊ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው 12 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃላይ በመክፈል ንብረቱን ከከፈለበት እና ንብረቱን እንዲያነሱ ግሩፑ ከሚያወጣው ፕሮግራም ጊዜ ጀምሮ በሚቆጠር 10 ተከታታይ የስራ ቀን ውስጥ ማንሳት ግዴታ ይኖርባቸዋል፣
  15. ማንኛውን ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ ሊብራራለት የሚፈልገው ነገር በሚኖርበት ጊዜ ጨረታው ከመዘጋቱ 5 ቀን በፊት በጽሁፍ ወይም በስልክ ቁጥር 0974304453 ደውሎ ሻጭ መስሪያ ቤትን መጠየቅ ይችላል፣ ኢ.ኢ.ግም የተጠየቀው ማብራሪያ ምላሽ የሚያስፈልገው መሆኑ ሲታመንበት የማስተካከያውን ማብራሪያ ሁሉም ተጫራጮች እንዲያውቁትና መጥተው እንዲወስዱ በመ/ቤቱ የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ይለጥፋል፣
  16. ግሩፑ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል መሆኑንና በከፊልም ሆነ በሙሉ ለመሰረዝ በህግ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማስታወሻ፡-

* ክፍያ የሚፈፀመው በኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ስም በተከፈተው ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1014900057975 እና አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ ሂሳብ ቁጥር 01325662239600 መሰረት ይሆናል፡፡

* ንብረቶቹ የሚገኙበት ቦታ አዲስ አበባ ከተማ (ሳሪስ ንፋስ ስልከ ፖሊ ቴክኒክት/ት ቤት ጀርባ በሚገኘው የዋና መ/ቤት ስቶር፣ ገርጂ አምበሳ ጋራዥ አጠገብ በሚገኘው የኢትዮ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ፣ ሜክስኮ ጠማማ ፎቅ የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ፣ ሳሪስ የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ፣ ደብረ ብርሃን የኮንስትራከሽን ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ፣ ፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ (ሳሪስ፣ ሞጆ፣ ታጠቅ፣ መካኒሳ)፣ ብረታ ብረት ፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪ (መካኒሳ (ባቱ)፣ ሳሪስ)፣ አዳማ የግብርና ማሽነሪ ኢንዱስትሪ (አዳማ) እና አቃቂ ቤዚክ ሜታልስ ኢንዳስትሪ ሲሆኑ ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች ከሚጫረቱበት ሎት ጋር የተያያዙ ስለተጫረቱበት ዕቃ የሚገልፅ ተጨማሪ ማብራሪያ በጨረታ ሰነዱ ላይ ይኖራል፡፡

* ከላይ ለተጠቀሰው አድራሻ፡-

 

ሻጭ

ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ

በግሩፑ በኩል የተወከለው

ንብረት አስወጋጅ አብይ ኮሚቴ

የቢሮ ቁጥር

Block-B ቢሮ ቁጥር 203

አድራሻ

ሜክሲኮ ከፌዴራል ፖሊስ ዋና መ/ቤት 300 ሜትር ዝቅ ብሎ

ከተማ/ክ/ከ

አዲስ አበባ ሜክሲኮ ልደታ ክ/ከ

ሀገር

ኢትዮጵያ

ስልክ ቁጥር

0974304453

 

 

ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ (ኢኢግ)

 

Save Tender