በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሪጅን ጽ/ቤት በያዘው በጀት ዓመት ለሪጅኑ ሠራተኞች የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሪጅን ጽ/ቤት/አሶሳ/
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሪጅን ለሪጅኑ ሠራተኞች የደንብ ልብስ ስፌት
አገልግሎት ግዥ ለመፈጸም የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር BGREU/NCB/03/18
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሪጅን ጽ/ቤት በያዘው በጀት ዓመት ለሪጅኑ ሠራተኞች የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በዚህ ጨረታ ላይ ለመሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች:
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡና በመስኩ ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና፣ በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ https://epg.ppa.gov.et ድረ- ገጽ ላይ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ EEU-BGREU ACC. (1000153727906) ገቢ በማድረግ የባንክ ስሊፕ በመያዝ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሪጅን ሰፕላይ ቼይን፣ ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ወይም ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 105/108 የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ EEU Benishangul Gumuze Region ተከፋይ የሆነ ብር 40,000.00/አርባ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴክኒካል ኮፒና ኦርጅናል ለየብቻ በማድረግ እንዲሁም ፋይናንሻል ኮፒና ኦሪጅናል ለየብቻ በማድረግ ሲፒኦ /CPO/ ኦሪጅናል ቴክኒካል ሰነድ ዉስጥ በመክተት አራቱንም በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ በማድረግ እስከ ተጠቀሰው የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ አሶሳ ከተማ አስተዳደር ፊት ለፊት በሚገኘው በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሪጅን ሰፕላይ ቼይን፣ ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ድረስ በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ጥር 5 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8:30 ላይ ይከፈታል።
- ሪጅኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር +251-57 275 4844 / 09 17 70 36 34 / 09 17 83 47 62 መጠየቅ ይችላሉ።
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሪጅን ጽ/ቤት/አሶሳ/
