የምዕራብ ኦሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት በስሩ ለሚገኙ መምሪያዎችና ጽ/ቤቶች አጠቃላይ ግዥ ለመፈጸም የግልጽ ጨረታ በማውጣት ለተጫራቾች ጥሪ ማድረግ ይፈልጋል።
በደ/ም/ኢ/ክ/መ/ የምዕራብ ኦሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የምዕራብ ኦሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት በስሩ ለሚገኙ መምሪያዎችና ጽ/ቤቶች አጠቃላይ ግዥ ለመፈጸም የግልጽ ጨረታ በማውጣት ለተጫራቾች ጥሪ ማድረግ ይፈልጋል። በዚህ መሠረት የመምሪያዎችና የጽ/ቤቶች የግዥ ፍላጐት መሠረት የግዥው ዓይነት እንዲሚከተለው በሎት አስቀምጧል።
|
ተ.ቁ |
የሎት ቁጥር |
የሎት ምድብ |
የጨረታ ማስታወቂያ CPO መጠን (በብር) |
ምርመራ |
|
1 |
ሎት 1 |
የተሽከርካሪ ጥገና |
50,000 |
|
|
2 |
ሎት 2 |
የደረቅ ጭነት አገልግሎት |
3,000 |
|
ከላይ በየሎት ምድብ የተጠቀሱትን ዕቃዎች ለማቅረብ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተቀመጡትን የመወዳደርያ መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል ።
ማሳሰቢያ፡-
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
- ለመንግስት ግዥ በአቅራቢነት ዝርዝር ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከደረጃ 3 እና ከዚያ በላይ ደረጃ ያላቸው ድርጅቶች ቀርቦ መወዳደር ይችላል።
- የመኪና ሊብሬ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- የመድን ድርጅት ኢንሹራንስ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል ፡፡
- የ2017 ዓመታዊ የአሽከርካሪ ምርመራ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- በየሎት ምድቡ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እውቅና ከተሰጣቸው ባንኮች የጨረታ ማስከበሪያ CPO ወይም ቢንድ ቦንድ /Bid Bond/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ የጥሪ ማስታውቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሠነድ በብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ ዞን ገቢዎች በመክፈል ከመምሪያው የግ/ን/አስር ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 07 በመውሰድ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ሁሉም ተጫራች የጨረታ ዶክመንቱን ኮፒ በማድረግ በፖስታ በማሸግ ማስገባት እንዲሁም በሰም ማሸግ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሳጥን የጨረታው ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ 15 የስራ ቀን ከሰዓት 9፡00 ሰዓት ታሽጎ በማግስቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡ 15ኛው ቀን ብሔራዊ ዝግ ቀን፣ ሀይማኖታዊ በዓል ወይም የስራ ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ታሽጎ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በሁሉም የጨረታ ሰነዶች ላይ የግርጌ ማህተም መምታት በዕቃ ዝርዝር ቦታ ላይ የመወዳደሪያ ዋጋውን መሙላት፤ ስልክ ቁጥር መመዝገብ እንዲሁም የተወዳደሩበት የዕቃ አይነት መመዝገብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች ይህ የጥሪ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት ተከታተይ ቀናት ውስጥ ጨረታ መወዳደርያ ዶክመንቶቹን በምዕራብ ኦሞ ዞን ፋይ/ስ/መመሪያ ቁጥር 07 ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃ (ሎት) መሠረት ውሉ በተመለከተ ለ45 /አርባ አምስት ቀናት/ ፀንቶ መቆየቱን ተወዳዳሪዎች በአጽኖት መረዳት ይኖርባቸዋል፡፡
መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኛ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0912368800/0967104693
አድራሻ፡- በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ/በምዕራብ ኦሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ/የምዕራብ ኦሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
ጀሙ
