የኦሮሚያ መሬት ቢሮ የመስሪያ ቤቱ ተሽከርካሪዎችን ከህጋዊ ጋራዥ አወዳድሮ ማስጠገን ይፈልጋል፡፡
Oromia Land Bureau (የኦሮሚያ መሬት ቢሮ)
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የኦሮሚያ መሬት ቢሮ የመስሪያ ቤቱ ተሽከርካሪዎችን ከህጋዊ ጋራዥ አወዳድሮ ማስጠገን ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መሥፈርቶች የሚያሟሉ ጋራዦችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- ተወዳዳሪዎች የዘመኑን ግብር የከፈሉና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና ውል ገብቶ በታባለው ጊዜ ውስጥ ተሽከርካሪዎችን ጠግኖ በጊዜ ጨርሶ ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN NO/ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር ሁለት መቶ (200 ብር) በመክፈል በኦሮሚያ መሬት ቢሮ 3ኛ ፎቅ ፋናንስ ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበርያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ለመወዳደር ዋጋ 150,000.00 /አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጥጋናውን የዋጋ ዝርዝር በጨረታ ማወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ስማቸውን፣ፊርማቸውንና አድራሻቸውን በማስፈርና ማህተም በማድረግ የጨረታ ዶክመንት ፋይናንሻል አርጅናልና ኮፒውን፣ ቴክኒካል አርጅናልና ኮፒውን እንዲሁም CPO በተለያየ (በአምስት ፖስታ) በታሸገ ኤንቨሎፕ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም በይገኙም ህዳር 2/2019 ዓ.ም ከቀኑ በ7፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሣጥኑ ከታሸገ ወይም ከተከፈተ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በዚህ ስልክ ቁጥር መጠቀም ይችላሉ 0946653304/094944572/ 0910622700/0919519951
አድራሻ፡- ሳርቤት አደባባይን ዞሮ ወደ ቄራ መሄጃ ዋናው አስፋልት 200 ሜትር ላይ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስሪያ ቤቶች ቅጥር ግቢ ውስጥ
የኦሮሚያ መሬት ቢሮ
✨ messages.ai_summary
The Oromia Land Bureau seeks a legal garage to repair its office vehicles. Eligible bidders must be tax-compliant, VAT-registered, hold a TIN, and be able to complete repairs on time. Bidders must submit technical and financial documents plus a CPO in separately sealed envelopes.
