በማ/ኢ/ክልል በየም ዞን የየም ተባበር ገ/ኅ/ሥራ/ኃ/የተ ዩኒየን በ2018 ዓ.ም ከጅቡቲ ወደብ እየቀረበ በዞኑ ዋና ከተማ በሳጃ ማዕከላዊ መጋዘን የሚከማቸውን የአፈር ማዳበሪያ ወደ ወረዳዎች በሚገኙ 19 ሽያጭ ጣቢያ መጋዘኖች ለማጓጓዝ በደረቅ ጭነት አገ/ት ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸው ባለንብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በየም ዞን የየም ተባበር ገበሬዎች ሕ/ሥራ ኃ.የተ.ዩኒየን /ሳጃ/
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር የምተ01/2018
በማ/ኢ/ክልል በየም ዞን የየም ተባበር ገ/ኅ/ሥራ/ኃ/የተ ዩኒየን በ2018 ዓ.ም ከጅቡቲ ወደብ እየቀረበ በዞኑ ዋና ከተማ በሳጃ ማዕከላዊ መጋዘን የሚከማቸውን የአፈር ማዳበሪያ ወደ ወረዳዎች በሚገኙ 19 ሽያጭ ጣቢያ መጋዘኖች ለማጓጓዝ በደረቅ ጭነት አገ/ት ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸው ባለንብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
ሎት |
የተፈለገው አገ/ት |
የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ |
|
1 |
አንድ |
ደረቅ ጭነት አገ/ት |
20,000.00 |
- የዩኒየኑን ሕገ-ደንብ የሚያከብርና ከማንኛውም ስነ ምግባር ችግር የፀዳ፤
- የተለያዩ የዘር ወቅት ሁኔታ፣ የጣቢያዎቹ ኮታ፣ የመጋዝን ጥበትና የመሳሰሉትን ችግሮች ታሳቢ በማድረግ የዞኑ ግብዓት ኮሚቴ የሚያስቀምጣቸውን ወቅታዊ አቅጣጫዎች ተቀብሎ ለማስተናገድ ፍቃደኛ የሆነና የመተባበር ባህርይ ያለው፤
- የአገ/ት ክፍያን በተመለከተ የጊዜ ገደብ እየሰጠ ተረጋግቶ ከሽያጭ ገቢ መቀበል የሚችል መሆን አለበት ፤
- በዘርፉ የታደሰ የሥራ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባና የዘመኑን የሥራ ግብር የከፈሉበት ማስረጃ፣ የተ.እ.ታ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN/ ዋናና ኮፒ በተለያዬ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታና የውል ማስከበሪያ የ20,000.00 ብር /CPO/ አሠርተው ማቅረብ አለባቸው።
- የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 200.00 ብር በመክፈል ወስደው በተዘጋጀው ቅጽ ላይ በግልጽ በአማርኛ ድልዝ ስርዝ ሳይኖርበት መጠየቂያውን ሙሉ በሙሉ በመሙላት በፖስታ በሚገባ አሽጎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ መክተት አለባቸው። የፈለጉትን ቦታ ብቻ መርጠው መሙላት አይቻልም።
- በሌላው ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻል።
- ዩኒየኑ ከማንኛውም ጨረታ አሸናፊ ጋር የራሱን አይሱዙ መኪና አሰማርቶ የማሠራት መብት አለው።
- የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን አንስቶ ለ15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት ላይ ታዛቢዎች ባሉበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም የተጫራቾች ያለመገኘት ጨረታ መክፈቻ ሥነሥርዓቱን አያተጓጎልም።
- የጨረታ አሸናፊ ወዲያው የሚገለጽ ቢሆንም ጨረታው በክልል ሲፀድቅ ቀርቦ ውል እንዲገባ በዩኒየኑ ጽ/ቤት ሲገለጽ ወዲያው ቀርቦ ውል በመግባት ማጓጓዝ አለበት።
- ጨረታውን ያላሸነፉት ጨረታው ከፀደቀ ወድያው ሰነዶቻውንና ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ይመለስላቸዋል።
- በጨረታው ላይ ቅሬታ ለማቅረብ የሚፈልግ ቅሬታውን ጨረታው በተከፈተ እስከ 3 ቀናት ውስጥ ብቻ ለየም ዞን ሕ/ሥራ ጽ/ቤትና ለዩኒየን ጽ/ቤት በጽሑፍ በማመልከቻ ማቅረብ ይችላል።
- ከ3 ቀናት በኋላ ከየትኛውም አቅጣጫ የሚቀርብ የቅሬታ አቀራረብ ተቀባይነት አይኖረውም፣
- ዩኒየኑ ሌላ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ወይም አስገዳጅ ሁኔታዎች ከገጠሙት ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የመመዝገቢያ ጊዜ፡- ይህ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ባሉት የሥራ ቀናት በሥራ ሰዓት በአካል በመቅረብ ይሆናል።
- መመዝገቢያ ቦታ ፡- በሳጃ ከተማ ከአ/አበባ ጂማ በሚሄደው አስፋልት ላይ 240 ኪ/ሜትር በየም ዞን ሕ/ሥራ ል/ጽ/ቤት ግብዓትና ግብይት ዳሬክቶሬት እና በፎፋ ለሚመዘገቡት በዩኒየኑ ጽ/ቤት ሂሳብ ክፍል ዘወትር ሥራ ሰዓት በአካል በመቅረብ ይሆናል፣
- ዩኒየኑ ጨረታውን የሚሰርዝበት አጋጣሚ ከተፈጠረ ለተጫራቾቹ ገንዘባቸውን ወዲያው ይመልሳል።
ለበለጠ መረጃ 09 10 29 27 80/ 09 42 35 69 24/ 09 13 19 72 19 ይደውሉ።
ቴሌግራም 09 52 19 86 03 ኢሜይል yemtebaberunion@.com
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በየም ዞን የየም ተባበር ገበሬዎች ሕ/ሥራ ኃ.የተ.ዩኒየን /ሳጃ/
