የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጐሮ ሰፈራ ጤና ጣቢያ ግዥ ቡድን ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጐሮ ሰፈራ ጤና ጣቢያ
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 002/2018 ዓ.ም
የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጐሮ ሰፈራ ጤና ጣቢያ ግዥ ቡድን ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
|
የሎት ቁጥር |
የዕቃው አይነት |
|
ሎት 1 |
ሶላር 6313 |
|
ሎት 2 |
የመስተንግዶ እና የሰራተኛ ካፍቴሪያ 6233/6216 |
ስለሆነም መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የሀገር ውስጥ ተጫራቾች አግባብነት ያለው በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የሀገር ውስጥ ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ከግብር ስብሳቢው ባለስልጣን ጨረታ ላይ መሳተፍ እንዲችሉ የተሰጠ ክሊራንስ /ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የሀገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ የሀገር ውስጥ ተጫራቾች የ2018 በጀት ዓመት የታደሰ የግብር ከፋይነት መለያ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሀገር ውስጥ ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ሎት 1 መስሪያ ቤቱ ባወጣው /specification/ መገለጫ የሚቀርብ ይሆናል፡፡
- ሎት 1 ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ጠቅላላ ዋጋ ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /C.P.O/ ብቻ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ሎት 2 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ብቻ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት ከሆነ ከአደራጃቸው አካል መደራጀታቸውንና በጨረታ ሥራ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ለእያንዳንዱ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ጐሮ ሰፈራ ጤና ጣቢያ አዲሱ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር በመውሰድ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው የሥራ ቀን 11፡00 ሰዓት ድረስ ጐሮ ሰፈራ ጤና ጣቢያ ግዥ ቡድን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫትን ያጠቃለለና ከላይ የተጠቀሱት ማስረጃዎች አሟልተው በታሸገ ኤንቨሎፕ ኮፒና ኦሪጅናል በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በተዘጋጀው ገሮ ሰፈራ ጤና ጣቢያ በግዥ ክፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን 4:00 ስዓት ታሽጎ 4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር በጐሮ ሰፈራ ጤና ጣቢያ አቢሲንያ ባንክ አጠገብ ያለው ፖሊስ ጣቢያ ገባ ብሎ ግዥ ከፍል አዲሱ ህንጻ ፲ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆነው የተገኙባቸውን ዕቃዎች ከአጠቃላይ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ የማስያዝና የግዥ ውል ስምምነት መፈፀም ይኖርባቸዋል፡፡
- በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት ከሆነ ካደራጃቸው አካል መደራጀታቸውና የጨረታ ዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርት ሳያሟሉ በጨረታ ላይ ለመሳተፍ መሞከር ከጨረታው ያሰርዛል፡፡
- መ/ቤቱ ጠቅላላ ለጨረታው ካቀረበው ብዛት 20% ከፍና ዝቅ ብሎ የግዥ ትእዛዝ ሊሰጥ ይችላል።
- ለጨረታው የተሰጠው ዋጋ ለ60 ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር ጐሮ ሰፈራ ጤና ጣቢያ አቢሲኒያ ባንክ አጠገብ ባለው ፖሊስ ጣቤያ ገባ ብሎ አዲሱ ሕንፃ 1ኛ ፎቅ በአካል በመምጣት ወይም ስልክ ቁጥር 0981-55-60-30 / 0981-55-80-30 በመደወል መረጃ መውሰድ ይችላሉ፡፡
የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጐሮ ሰፈራ ጤና ጣቢያ
