የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በ2018 በጀት ዘመን የሚገለገልባቸውን ተሽከርካሪዎች ለማስጠገን በሀዋሳ ከተማ የሚገኙ ጋራዦችን በጨረታ በማወዳደር ለአንድ ዓመት የሚቆይ የጥገና የእጅ ዋጋ ደንበኛ ለመያዝ ይፈልጋል፡፡
South Radio and Television Agency (የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት)
ሁለተኛ ዙር በድጋሚ የመጣ የተሽከርካሪ ጥገና
ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 001/2018
የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በ2018 በጀት ዘመን የሚገለገልባቸውን ተሽከርካሪዎች ለማስጠገን በሀዋሳ ከተማ የሚገኙ ጋራዦችን በጨረታ በማወዳደር ለአንድ ዓመት የሚቆይ የጥገና የእጅ ዋጋ ደንበኛ ለመያዝ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች፡-
- ተጫራቾች በሥራ መስኩ የተሰማሩና የተሸከርካሪ ጥገና ጋራዥ የብቃት ማረጋገጫ ለቀላል ሁለገብ ጥገና እንዲሁም ለመካከለኛና ለከባድ ተሽከርካሪ ጥገና 3ኛ ደረጃ እና ከዚያ በላይ ደረጃ ያገኙና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በሀገር ውስጥ አገልግሎት ሰጪዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው የተሰጠ ማስረጃ፣ በሥራ መስኩ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ፣ የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸውና በጨረታ ላይ እንዲሳተፉ የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ቼክ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (guaranty) ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ኮፒ በመያዝ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ወደ ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት (ቢሮ ቁጥር 10) ቀርበው የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት (ቢሮ ቁጥር 10) የጨረታ ሰነድ መውስድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ቴክኒካልና ፋይናሻል ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ሁለቱንም በአንድ እናት በሰም በታሸገ ኢንቬሎፕ ውስጥ በማድረግ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስራ አምስተኛ የሥራ ቀን ድረስ በመ/ቤታችን ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው የስራ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጠዋት 3:00 ሰዓት ታሽጎ 3፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ 0462125541/ 0462204750/ 0462201091 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት
