የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሸገር ሪጅን ጽ/ቤት በሪጅኑና በሥሩ በሚገኙ አገልግሎት መስጫ ማእከላት ተከማችተው የሚገኙ ከታች በሠንጠረዡ የተዘረዘሩትን ያገለገሉ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሸገር ሪጅን ጽ/ቤት
ያገለገሉ እቃዎች ሽያጭ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ኢ/ኤ/አ/ሸገ/ሪጅ/ግ/ጨ/02/2018
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሸገር ሪጅን ጽ/ቤት በሪጅኑና በሥሩ በሚገኙ አገልግሎት መስጫ ማእከላት ተከማችተው የሚገኙ ከታች በሠንጠረዡ የተዘረዘሩትን ያገለገሉ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብ ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡
|
ሎት |
የእቃው ዓይነት |
የሚገኝበት ቦታ |
መለኪያ |
ብዛት |
የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ |
|
1 |
የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረቶች እና የድራም ብረቶች (ለአቅላጭ ፋብሪካዎች ብቻ) |
ሸገር ሪጅን ጽ/ቤት እና ቢሾፍቱ አገ/መ/ማ |
ኪ.ግ |
20,000 |
ታህሳስ 24 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት |
ታህሳስ 24 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡30 ሰዓት |
ብር 50,000 .00 (ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ) |
|
2 |
ያገለገሉ አሮጌ የከባድ እና ቀላል ተሽከርካሪ ጎማዎች |
ሸገር ሪጅን ጽ/ቤት እና ቢሾፍቱ አገ/መ/ማ |
በቁጥር |
574 |
ብር 30,000 .00 (ሰላሳ ሺህ ብር ብቻ) |
||
|
3 |
ባዶ የዘይት በርሜሎች |
ሸገር ሪጅን ጽ/ቤት እና ቢሾፍቱ አገ/መ/ማ |
በቁጥር |
200 |
ብር 40,000 .00 (አርባ ሺህ ብር ብቻ) |
||
|
4 |
አሮጌ ተመላሽ የእንጨት ምሰሶዎች |
ጣፎ፣ ሱሉልታ እና ቢሾፍቱ |
በሜ.ኪ |
484 |
ብር 20,000 .00 (ሃያ ሺህ ብር ብቻ) |
- ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በድርጅታችን አካውንት ቁጥር (EEU Finfine Zuria District Account No. 1000482105592) የማይመለስ ብር 350 /ሶስት መቶ ሀምሳ ብር/ ለእያንዳንዱ ሎት ገቢ በማድረግ ዘወትር በሥራ ሰዓት 22 ድንበሯ ሆስፒታል ፊት ለፊት የሪጅኑ ዋና መ/ቤት ሸገር ሪጅን ሰፕላይ ቼይን እና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ በመምጣት የሚወገዱትን ንብረቶች ዝርዝር መረጃ የያዘ የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነድ ገዝተው ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት፤ ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ በመሄድ መመልከት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን ከላይ በሠንጠረዡ ውስጥ በተገለፀው መሠረት ሆኖ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ለስድስት ወራት የሚያገለግል የባንክ ዋስትና (Bid Bond) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታ ቁጥር ኢ/ኤ/አ/ሸገ/ሪጅ/ግ/ጨ/02/2018 የሚል ምልክት በማድረግ እንዲሁም የተወዳደሩበትን ሎት በመግለጽ ከላይ በተጠቀሰው ቀን፤ ሰዓት እና አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታው በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት/ባይገኙም የሪጅኑ ዋና መ/ቤት ሸገር ሪጅን ሰፕላይ ቼይን እና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ይከፈታል፣
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር +251-011-6-36-61-05 መደወል ይችላሉ።
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሸገር ሪጅን ጽ/ቤት
