በደ/ም/ኢ/ሕ/ከልላዊ መንግስት ካፋ ዞን ሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ገቢ/ንግድ ክላስተር ጽ/ቤት በከተማ አስተዳደር ውስጥ ሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቢሮ ግንባታ ለማስገንባት ይፈልጋል።
በደ/ም/ኢ/ሕ/ክልላዊ መንግስት ካፋ ዞን ሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ገቢ ንግድ ክላስተር
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 2/2018
በደ/ም/ኢ/ሕ/ከልላዊ መንግስት ካፋ ዞን ሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ገቢ/ንግድ ክላስተር ጽ/ቤት በከተማ አስተዳደር ውስጥ ሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቢሮ ግንባታ ለማስገንባት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት ተጫራቾች ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- የVAT ተመዝጋቢ፣ TIN ቁጥር፣ የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው እና ጨረታ እንዲሳተፉ ከገቢዎች የሚሰጥ ደብዳቤ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና በመ/መ/ቤት አቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማስረጃ አያይዞ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ደረጃ 6 BC/GC እና ከዚያ በላይ የሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችልና የሥራ ፍቃዱ በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር እና በክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሕጋዊ ማረጋገጫ የተሰጠው መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ሆኖ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ30 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 800 /ስምንት መቶ ብር/ እየከፈሉ ከሺሸንዳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ገቢ ንግድ ክላስተር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ላይ ዘወትር በሥራ ሰዓት የድርጅታቸውን ዶክመንት ኮፒ ይዘው በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን መወዳደሪያ ኦርጅናል ቴክኒካልና ፋይናንሻል ከሁለት ሁለት ኮፒዎች ጋር ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በካፋ ዞን ሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ገቢ ንግድ ክላስተር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፣
- እያንዳንዱ ተጫራቾች መወዳደር የምችሉት ከሥራ ፍቃዳቸው ውጭ መወዳደር እና የሌላውን ተወዳዳሪ ተንተርሶ ዋጋ መሙላት አይቻልም።
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዋጋ 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ገቢ ንግድ ክላስተር ጽ/ቤት ስም ማስያዝ አለባቸው። ጨረታ በ31ኛ የሥራ ቀናት ከጧቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት ይታሸጋል በዕለቱ ከሰዓት 8፡00 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ሕጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ተወካዮቻቸው ያለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም።
- የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን (CPO) ለተሸናፊው ወዲያውኑ የሚመለስ ሲሆን አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን አንስቶ እስከ 7ኛው ቀን ድረስ ውሉን የማይፈጽም ከሆነ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል።
- የጨረታው መዝጊያና መከፈቻ የሥራ ቀናት ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0476680500/0917950945 በመደወል መረዳት ይቻላል።
በደ/ም/ኢ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ካፋ ዞን ሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ገቢ/ንግድ ክላስተር ጽ/ቤት
