በሚድሮክ ኢትዮጵያ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር የአፐር አዋሽ አግሮ ኢንዱስትሪ ያገለገሉ ልዩ ልዩ ንብረቶችን በጨረታ አወዳድሮ ባለበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል።
UPPER AWASH AGRO-INDUSTRY ENTERPRISE (አፐር አዋሽ አግሮ ኢንዱስትሪ)
ያገለገሉ ንብረቶች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
በሚድሮክ ኢትዮጵያ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር የአፐር አዋሽ አግሮ ኢንዱስትሪ ያገለገሉ ልዩ ልዩ ንብረቶችን በጨረታ አወዳድሮ ባለበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል።
በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች
- ተጫራቾች የተሰማሩበትን የሥራ መስክ የሚገልፅ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን እና ለተጨማሪ እሴት ታከስ የተመዘገቡበትን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል
- ንብረቶቹን ለመግዛት ካቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ 20% በኢንዱስትሪው ስም (ሚድሮክ ኢትዮጵያ ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር አፐር አዋሽ አግሮ ኢንዱስትሪ) በተዘጋጀ ሲፒኦ የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ወይም በጨረታ ማስገቢያ ሰዓት ከማለቁ በፊት የማቅረብ ግዴታ አለበት። ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ዋስትና የጨረታው ውጤት ሲታወቅ ወዲያው ይመለስላቸዋል።
- ተጫራቾች ዕቃውን በሙሉ ወይም በከፈል መጫረት ይችላሉ።
- ተጫራቾች እያንዳንዱን ያገለገሉ ንብረቶች የሚገዙበትን ዋጋ የሚያስገቧቸውን ሰነዶች በአግባቡ በታሸገ ኢንቬሎፕ (ፖስታ) መርቲ በሚገኘው ዋናው ጽ/ቤት ወይም አዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ መካኒሳ አቦ ፊት ለፊት ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሕንፃ 6ኛ ፎቅ ላይ የሚገኘው የኢንዱስትሪው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ወይም አዳማ መብራት ኃይል ብርቄ ደስታ ሕንፃ ጠበቃ ፍሬ ሕይወት ወዬሳ ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ አስመዝግበው ማስገባት አለባቸው።
- ከንብረቶቹ ሽያጭ በኋላ ያሉ ማናቸውም ወጪዎች በገዢው (በአሸናፊው) ይሸፈናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን ያገለገሉ ንብረቶች ጨረታ ብለው ጽፈውበት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ30ኛው ቀን ማስገባት አለበት 30ኛው ቀን ሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ የጨረታውን ሰነድ ማስገባት ይቻላል። ጨረታው በዕለቱ ከጧቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም ኢንዱስትሪው ጨረታውን የመከፈት መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የሚሸጡ ንብረቶችን የሚያሳይ ሰነድ ለኢንዱስትሪው ብር 500 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ። ሰነዱ የሚሸጥበት ቦታ
- ዋና ጽ/ቤት መርቲ ጀጁ ስልክ 0221122707/0913387848
- አዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ መካኒሳ አቦ ፊት ለፊት ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሕንፃ 6ኛ ፎቅ ላይ የሚገኘው የኢንዱስትሪው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ስልክ ቁጥር 091408605/0930984925
- አዳማ መብራት ኃይል ብርቄ ደስታ ሕንፃ ጠበቃ ፍሬ ሕይወት ወዬሳ ቢሮ ቁጥር 4 ስልክ 0910936614
❖ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ኢንዱስትሪው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አፐር አዋሽ አግሮ ኢንዱስትሪ
