ኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤንድ ዴቨሎፕመንት አሶሴሽን የበጎ አድራጎት ድርጅት የገቢና ወጪ መግለጫዎች በውጭ ኦዲተር ማስመርመር ይፈልጋል፡፡
Elshadai Relief and Development Association (ኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤን ዴቨሎፕመንት አሶሴሽን)
የጨረታ ማስታወቂያ
ኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤንድ ዴቨሎፕመንት አሶሴሽን የበጎ አድራጎት ድርጅት የገቢና ወጪ መግለጫዎች በውጭ ኦዲተር ማስመርመር ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ የውጭ ኦዲተሮች በጨረታው እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል፡፡
መስፈርቶች
- የ2017 ዓም የታደሰ ሙያ እና የንግድ ፍቃድ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለውና የተ.ዕ.ታ ተመዝጋቢ የሆነ
የኦዲት ሥራው ጠቅላላ ወሰን
- የውጭ ኦዲተሩ የድርጅቱን እ.ኤ.አ 2024 እና 2025 በጀት ዓመት ሙሉ የሂሳብ መዝገብ (የገቢና ወጪ፣ የሀብትና ዕዳ እና ገንዘብ ፍሰት መግለጫዎችን ኦዲት የሚያደርግ ይሆናል፡፡
- ጠቅላላ ኦዲት የሚደረጉ የድርጅቱ ቦክስ ፋይሎች ብዛት 3 ናቸው
- ኦዲተሩ ኦዲቱን ማካሄድ ያለበት ጠቅላላ ተቀባይነት ባለው የሒሳብ መርሕ እና በድርጅቱ የሂሳብ መመሪያ መሠረት ይሆናል፡፡
በዚህ መሠረት ከላይ የተቀመጡትን የምታሟሉ የውጭ ኦዲተሮች ፕሮፎርማችሁን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ ሰባት የሥራ ቀናት ሀያት ዞን አምስት በሚገኘው ዋና መቤታችን በአካል በመቅረብ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን በስ.ቁ 09-11 79 39 58 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤን ዴቨሎፕመንት አሶሴሽን
