Tender Detail

Tender Details

  • Company Kombolcha College of Agriculture (ኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ)
  • Address ኮምቦልቻ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0335510186
  • Website
  • Deadline05 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security1%
  • opening date2026-01-05 00:00:00
  • Categories Food Items And Drinks

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ ለ2018 የበጀት ዓመት ተቀብሎ ለሚያስተምራቸው ተማሪዎች ለምግብ አገልግሎት የሚውል አቅርቦት እና የተለያዩ እቃዎችን አወዳድሮ በጨረታ መግዛት ይፈልጋል

Kombolcha College of Agriculture (ኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ)


በድጋሜ የወጣ የብሄራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ ለ2018 የበጀት ዓመት ተቀብሎ ለሚያስተምራቸው ተማሪዎች ለምግብ አገልግሎት የሚውል አቅርቦት አወዳድሮ በጨረታ መግዛት ይፈልጋል። ለተማሪዎች የምግብ አቅርቦት ማለትም፡- ሎት 1፣ የተለያዩ አትክልቶች (ቀይ ሽንኩርት፣ነጭ ሽንኩርት፣ቃሪያ፣ የወጥ ድንች ጥቅል ጎመን እና ካሮት) ሎት2-፡ የባልትና ውጤቶች (አተር ክክ ፣ምስር ክክ፣ ምጥን ሽሮ ፤ በቂ ቅመም ያለው የተዘጋጀ በርበሬ እና የተፈጨ ጎመንዘር) ሎት 3፡- ዳቦ ሎት4፡- ሸተጣሸቀጥ (ተማሪም ድልህ/ ሳልሳ/850ግራም፣ኛ ደረጃ ሩዝ፤ ፖስታ ባለ 500 ግራም የምግብ ጨው፣ ማርማላታ፣ሻይ ቅጠል ባለ100 ግራም) ሎት5፡- የተፈጨ የበሬ ስጋ ፤ ሎት6፡- ሰርገኛ ጤፍ( ወዝ ያለው 1ኛ ደረጃ የሆነ) ሎት7፡- ተፈልጦ ተዘጋጀ የባህርዛፍ እንጨት ማገዶ የሚውል ሎት8፡- በኤሌክትሪክ የሚሰራ የእህል ወፍጮ ተከላ የሚውሉ እቃዎችን፣ የመጋገሪያ ማሽንና ሽንኩርት መፍጫ ሎት9፡- የተሽከርካሪ ጎማና መለዋወጫ እቃዎች ሎት10፡- የውሃ መስመር መለዋወጫ እቃዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምችሉ መሆኑን ኮሌጁ ይጋብዛል።

  1. ከላይ ከሎት 1 እስከ ሎት 10 የተዘረዘሩትን አቅርቦቶች ለማቅረብ አግባብ የሆነ፣ በየዘርፉ እና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ በደንብ በሚነበብ ፎቶ ኮፒ ከሰነዱ ጋር በተናጥል A4 ወረቀት በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልፀውንና በየዘርፉ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በብር 200/ሁለት መቶ/ በመከፈል ከኮሌጁ ቢሮ ቁጥር 10 መግባት ይቻላል። በጨረታ ሰነዱ ላይ ዋጋ ያልተሞላበት ክፍት ቦታ ካለ፣ጨረታ ሰነዱ በፍሎድ ከተነካ እንዲሁም ስርዝድልዝ ካለና ፓራፍ ካላደረገ ከጨረታ ውድቅ ይሆናሉ። የግዥ መጠን ከ200,000 በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ሰርትፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ከአንድ ዘርፍ በላይ ለምትሳተፉ ተጫራቾች ለየብቻው የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከታወቁ ባንኮች የሚሰጥ እንደተጫራቹ ምርጫ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተርኦፍ ክሬድት ወይም በጥሬ ገንዘብ ሆኖ የጠቅላላ ዋጋ ግምት 1% ቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባችኋል። ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ ለየብቻ ማስያዝ ሲኖርባቸው የሁሉንም ሎቶች ደምሮ በአንድ ላይ የሚያስይዝ ተጫራች ካለ ከጨረታ ውጭ ይሆናል። ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑ ይታወቅ።
  4. ውድድሩ የሚካሄደው በእያንዳንዱ ሎት ድምር መሆኑ ይታወቅ። አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸለት በኋላ የሞላውን የጠቅላላ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ በፍትህ ጽ/ቤት ቀርቦ ውል ለመውሰድ ፈቃደኛ መሆን አለበት። የጨረታው ዋጋ ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ለ40 ቀናት ይሆናል።
  5. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 27/4/2018 ዓ.ም ከተኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 12 ዘወትር በስራ ሰዓት በጥሩ ሁኔታ በታሸገ በ2 /ሁለት/ ፖስታ ኮፒ እና ኦርጅናል በማለት የድርጅታቸውን ማህተም እና ፊርማ በማድረግ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታውም በዚሁ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት በኮሌጁ ቅጥር ግቢ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾች ካልተገኙ ጨረታው ከመከፈት አይታገድም ።
  6. በጨረታውለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾችተጨማሪመረጃከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0335510186/0335514206 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
  7. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

 

ኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ (ወሎ)

Save Tender