Tender Detail

Tender Details

  • Company ካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ (ቦንጋ)
  • Address ቦንጋ : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0473311826
  • Website
  • Deadline03 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Securityለሎት1 ለሎት.2. እና፣ ለሎት3- ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ እና ለሎት.4. ብር 300,000.00 /ሦስት መቶ ሺህ ብር/
  • opening date2026-01-03 00:00:00
  • Categories Wood And Wood Working , Vehicle (Garage Service) , Electronics Materials , Vehicle tire , Forest And Tree Sales

ካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ (ቦንጋ) ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት እቃዎች እና አገልግሎቶች ህጋዊ ከሆኑ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል።

ካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ (ቦንጋ)


 

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር-ግ/ጨ/05/2018

 

የካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በሎት በመከፋፈል 2018 በጀት ዓመት በዞን ማዕከል ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ማለትም ሎት-1- ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ለመግዛት ለ2ተኛ ጊዜ የወጣ ፣ ሎት -2- የተለያዩ ሞዴል ላላቸው ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚውል የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማና ካላማንዳሪ ለመግዛት፣ ሎት 3- የተለያዩ ተሸከርካሪ ጥገና አገልግሎት ጋራዥ እና ሎት 4- በካፋ ዞን ፖሊስ መምሪያ አማካይኝነት በጊምቦ ወረዳ ዳካ ቀበሌ እና በካፋ ዞን ፖሊስ በህገ ወጥነት የተያዙ የሰው ሠራሽ ደን ዛፍን ለመሸጥ ለሦስተኛ ጊዜ የወጣ እስከ በጀት ማቢቂያ ድረስ ማለትም ሰኔ 30/2018 ዓ/ም ዋጋ ፀንቶ የሚቆይ ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት፣

  • ሎት 1. ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ለመግዛት፤
  • ሎት 2. የተለያዩ ሞዴል ላላቸው ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚውል የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማና ካላማንደሪ ለመግዛት፣
  • ሎት 3. የተለያዩ ተሽከርካሪ ጥገና ጋራዥ አገልግሎት ለመግዛት
  • ሎት 4. በካፋ ዞን ፖሊስ መምሪያ አማካይኝነት በጊምቦ ወረዳ ዳካ ቀበሌ በህገ ወጥነት በካፋ ዞን ፖሊስ የተያዙ የሰው ሠራሽ ደን ዛፍን ለመሸጥ ለሦስተኛ ጊዜ የወጣ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ ለማወዳደር ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ፡-

የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ፣ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ የአቅራቢነት ሰርቴፊኬት፣ የቲን /TIN/ ከገቢዎች ግብር ስለመክፈላቸው የተሰጠ ማስረጃ እና የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

ተጫራቾች ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች የጨረታ ዶክመንት ሊገዙ ሲመጡ ኦርጅናሉን እና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ አቅርበው እንዲመሳከር የማድረግ ግዴታ አለባቸው፡፡

ተጫራቾች ለሁሉም ሎቶች ለእያንዳንዳቸው የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ ካፋ ዞን ገቢዎች ባለስልጣን ቅ/ጽ/ቤት ቀርቦ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ለተከታታይ አስራ አምስት /15/ ለተከታታይ ቀናት ካፋ ዞን ፋይናንስ መመሪያ ግዥ ንብ/አስ/ሥራ ሂደት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

ተጫራቾች የጨረታ ማሰከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO (Certified payment order)፣ ጥሬ ገንዘብ ወይም ቼክ ለሎት1 ለሎት.2. እና፣ ለሎት3- ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ ከቴክኒካል ፖስታ ውስጥ በማስገባት እና ለሎት.4. ብር 300,000.00 /ሦስት መቶ ሺህ ብር/ በካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥ ንብ/አስ/ ስም በማሰራት ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ለሎት1፣ ለሎት2 እና ለሎት-3- ተጫራቾች ፋይናንሻል እና ቴክኒካል የጨረታ ዶክመንት ተገቢውን ፊርማ እና ማህተም በማሳረፍ ለየብቻ እንዳንድ በሰም/በሙጫ/ በታሽጉ ፖስታዎች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት እና ሌላው ደግሞ ለሎት.4. ተጫራቾች የጨረታ ዶክመንት ተገቢውን ፊርማ እና ማህተም በማሳረፍ በሰም/በሙጫ/ በታሸጉ ፖስታዎች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት በካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥ ንብ/አስ/ በመቅረብ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡

የጨረታው ሳጥን ሁሉም ሎቶች በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4:00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ከጠዋቱ በ4:30 ሰዓት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል። በመክፈቻው ዕለት የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮች ያለመገኘት የጨረታ መክፈት ሂደት አያስተጓጉልም። 15 ተከታታይ ቀናት የተባለው ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም በዓላት ቀን ጨምሮ የሚቆጠር ነው።

ተጫራቾች በሎት 3፣ የተለያዩ የተሽከርካሪዎች ጥገና አገልግሎት ጋራዥ ለመወዳደር ደረጃ 3 ፍቃድ እና የዘመኑን የጋራዥ ኢንሹራንስ ማቅረብ አለባቸው፡፡

ሎት 4- አሸናፊ ድርጅት ጨረታውን ያሸነፈበትን ጠቅላላ ድምር ዋጋ ከካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በሚገለፀው የባንክ ሂሳብ ቁጥር ግቢ በማድረግ ያሸነፋቸውን የደን ዛፎችን በራሱ ወጪ በማስጫን በ30 ቀን ውስጥ ሙሉ በሙሉ ማንሳት ይጠበቅባቸዋል።

ሎት 4 ተጫራቾች ለሽያጭ የተዘጋጁ ሁሉንም የሰው ሠራሽ ደን ዛፍ እንጂ በተናጠል የሚፈልጉትን መወዳደር ከጨረታ ውጭ ያደርጋል።

ሎት -4- ገዢ በጨረታ ያሸነፈውን የደን ክልል ከተረከበ በኋላ እንዲቆረጥ የተፈቀደለትን የደን ክልል ያመረተውን ምርት የማስጠበቅ ኃላፊነት የራሱ ይሆናል።

ሎት 4 ለተጫራቾች የጨረታ ማሰከበሪያ ያስያዙት CPO ፣ጥሬ ገንዘብ እና ቼክ ተመላሽ የሚደረገው ያሸነፉትን ዛፎችን ሙሉ በሙሉ ማንሳታቸው ሲረጋገጥ መሆኑን ታውቆ በወቅቱ ካልተነሳ ለጨረታ ማሰከበሪያ ያስያዙት CPO፣ጥሬ ገንዘብ እና ቼክ የሚወረስ ይሆናል።

ተጫራቾች ሁሉንም ሎቶች ያሸነፉበትን የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ /performance bond/ ለማስያዝ ፈቃደኛ መሆን አለባቸው፡፡

ተጫራቾች አሰሪው መ/ቤት ያዘጋጀውን የተጫራቹን መመሪያ እና የቴክኒካል ዶክመንት መጠይቅ ማሟላት ይጠበቅባቸዋል። አሸናፊው ድርጅት ከላይ ሎት -1- እና ለሎት2 የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በባለሙያ በማስፈተሽ በሙሉ በራሱ ወጪ ካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ንብረት ክፍል አቅርቦ የማስረከብ ግዴታ አለበት።

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0473311826 መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

ካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ (ቦንጋ)

Save Tender