በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ-7 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት አመት 2ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ ግዥ አላቂ የጽህፈት እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ ኮምፒውተር ጥገና፣ የደንብ ልብስ ስፌት፣ ኤሌክትሮኒክስ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 7 ፋይናንስ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር /002/2018
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ-7 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት አመት 2ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ ግዥ አላቂ የጽህፈት እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ ኮምፒውተር ጥገና፣ የደንብ ልብስ ስፌት፣ ኤሌክትሮኒክስ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች ያለውን መስፈረት የምታሟሉ አመልካቾች መወዳደር ትችላላችሁ።
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድና የዘመኑ ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የቫት /VAT/ ተመዝጋቢ የሆናችሁ
- ተጫራጮች ለሚጫረቱባቸው እቃዎች በሙሉ ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ናሙና ማቅረብ ለማይጠበቅባቸው እቃዎች ብቻ በፎቶ የተደገፈ መሆን አለበት ናሙናዎቹንም ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ማስገባት አለባቸው። ያስገቧቸውን ናሙናዎች እስከ ስድስት /6/ ወር ድረስ መልሰው ካልወሰዱ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
- የመንግስት ግዥ አስተዳደር የግዥ አቅራቢነት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል።
- አንዱ በሌላው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከታች በሰንጠረዡ በእያንዳዱ ሎት ለየብቻ መሰረት በባንክ በተረጋገጠው ሲፒኦ /CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው። ሲ.ፒ.ኦ /CPO/ ከኦርጂናል ሰነድ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት።
|
ተ.ቁ |
የጨረታ አይነት |
የሎት ዝርዝር |
ማስያዝ ያለባቸው የሲ.ፒ.ኦ የብር መጠን |
|
1 |
አላቂ የጽህፈት እቃዎች |
ሎት-1 |
10,000.00 |
|
2 |
የጽዳት እቃዎች |
ሎት-2 |
25,000.00 |
|
3 |
የደንብ ልብስ |
ሎት-3 |
15,000.00 |
|
4 |
ኮምፒውተር ጥገና |
ሎት-4 |
5,000.00 |
|
5 |
የደንብ ልብስ ስፌት |
ሎት-5 |
3,000.00 |
|
6 |
ኤሌክትሮኒክስ ግዥ |
ሎት-6 |
25,000.00 |
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ በመንግስት የሥራ ሰዓት ለእያንዳንዱ የጨረታ አይነቶች በሎት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዋጋ 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን የቢሮ ቁጥር 15 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
- በጥቃቅን አነስተኛ የተደራጁ ልዩ አስተያየት የሚደረግላቸው ራሳቸው ባመረቱት ምርት ላይ ብቻ ሲሆን ከዚህ ውጪ እንደማንኛውም ተጫራች የሚታዩ ይሆናል። ከተደራጁበት ለወረዳችን መደራጀታቸውን የሚገልጽ እና አምራች ለሆኑት ብቻ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ሁሉንም የጨረታ ሰነዱን በመሙላት ኦርጂናል እና ኮፒውን ለየብቻ ታሽጎ በሚመለከተው ኃላፊ ተፈርሞ እና የድርጅቱን ማህተም ያረፈበት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ዋጋ ሲሞሉም የቫት /VAT/ ዋጋን ጨምሮ ማካተት አለበት። ነገር ግን ለአገልግሎት ግዥ ለሆኑት ቲኦቲ ተመዝጋቢ ቢሆኑም መወዳደር ይችላሉ።
- ጽ/ቤቱ የሚገዛቸው ግዥዎች ከውል በፊት የእቃውን ብዛት በ20% መጨመርም ሆነ መቀነስ ይችላል።
- ተጫራቾች ባሸነፉት አጠቃላይ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- አሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፏቸውን እቃዎች በውላቸው መሰረት ሙሉ በሙሉ በራሱ ትራንስፖርት ጽ/ቤት ድርስ ንብረት ክፍል ገቢ የማድረግ ግዴታ አለባቸው።
- ሎት 4 (አራት) ለአንድ አመት ውል ለመግባት ፍቃደኛ የሆነ
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ10ኛው ቀን በእለቱ 11፡30 ታሽጎ በማግስቱ በ11ኛው ቀን 3፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ሆኖም ግን ተጫራቾች ባይገኙም በመመሪያው መሰረት ይከፈታል፣ ነገር ግን የመንግሥት ሥራ በማይኖርበት በመንግስት መገናኛ ብዙኃን በግልጽ የተረጋገጠ ቀን ከሆነ በሚቀጥላው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ይከፈታል።
- አሸናፊ ተጫራች አሸናፊነታቸው በደብዳቤ በተገለፀላቸው 7 የቅሬታ ቀናት ካለቀ በኋላ ከ8-15 ባሉት ቀናት ውስጥ ውል መዋዋል አላባቸው።
- መስሪያቤቱ (ወረዳው) በጨረታ የተሻለ አማረጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታ ማስታወቂያ ያልተገለጹ ካሉ በግዥ መመሪያ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ።
- ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ ለ 60 ቀን ይሆናል።
አድራሻ፡- ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር አዲሱ ገበያ ወደ ቀጨኔ በሚያስኬደው መንገድ 200 ሜትር ገባ ብሎ ሀምሌ 19/67 ት/ቤት አጠገብ
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0111-27-52-65 /0111-26-81-79/
በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ-7 ፋይናንስ ጽ/ቤት
