Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጉለሌ ክ/ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት ስር የሚገኘው የምዕራፍ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ከመደበኛ በጀት እና ከድጎማ በጀት አንዲሁም ከውስጥ ገቢ በመንግስት ገዥ መመርያ መሰረት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውል የትምህርት መገልገያ መሳርያዎችን በሁለተኛ ዙር ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የምዕራፍ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 002/2018

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጉለሌ ክ/ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት ስር የሚገኘው የምዕራፍ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ከመደበኛ በጀት እና ከድጎማ በጀት አንዲሁም ከውስጥ ገቢ በመንግስት ገዥ መመርያ መሰረት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውል የትምህርት መገልገያ መሳርያዎችን በሁለተኛ ዙር ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የምዕራፍ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ከፍል መውሰድ ትችላላችሁ፡፡

 

ተ.ቁ

የአቃው አይነት

ኮድ

ሎት

የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና

1

የደንብ ልብስ

6211

1

1,302

00

2

አላቂ የቢሮ እቃዎች

6212

2

373

00

3

ህትመት

6213

3

476

00

4

የህክምና ዕቃ

6214

4

466

00

5

አላቂ የትምህርት ዕቃዎች

6215

5

500

00

6

አላቂ የፅዳት እቃዎች

6218

6

1,559

00

7

ልዩ ልዩ

6219

7

1,428

00

8

የሰራተኛ መስተንግዶ

6233

8

6,159

00

9

የተለያዩ ጥገናዎች

6244

9

4,500

00

10

ቋሚ እቃ

6313

10

4,500

00

 

  1. የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል እና የዘመኑ ግብር የከፈለ፡፡
  2. በዘርፉ የተሰማሩበት ንግድ ፍቃድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. አቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
  4. የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
  5. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ ቫትን ጨምሮ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልፅ ማስፈር እና መጨረሻ ቦታ ላይ ፊርማ እና ማህተም በመምታት በ 1 ኦርጅናል እና 1 ኮፒ አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ የሆኑባቸውን እቃዎች ከአጠቃላይ ዋጋ 10 ፐርሰንት የውል ማስከበርያ በማስያዝ እና የግዥ ውል ስምምነት መፈፀም ይኖርባቸዋል።
  7. አሸናፊው ድርጅት የትራንስፖርት ወጭ በራሳቸው እስከ ት/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታ የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በወጣበት 10ኛው ቀን 10፡30 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 በት/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል ይከፈታል፡፡
  10. እያንዳንዱ ተጫራች የዕቃዎችን ናሙና /ሳምፕል/ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  11. የውል ማስከበርያም ሆነ የጨረታ ማስከበርያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  12. ትምህርት ቤቱ እንደ አስፈላጊነቱ የእቃውን መጠን ከውል በፊት 20 % መጨመር እና 20% የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  13. ተጫራቾች በጥቃቅን እና አነስተኛ የምትወዳደሩ አምራቾች (ተጨማሪ እሴት) ያላቸው መሆን አለባቸው። በዚሁ መሰረት ልዩ አስተያየት የሚደረግላቸው መሆኑን እየገለፅን ካደራጃቸው ተቋም ይህን የሚገልፅ የድጋፍ ደብዳቤ እንድታቀርቡ እንጠይቃለን፡፡
  14. ትምህርት ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

አድራሻ፡- አዲስ አበባ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አንበሳ ጋራዥ በስተጀርባ ወይም ከዊንጌት ወደ አዲሱ ገበያ በሚወስደው መንገድ በስተቀኝ ከፍ ብሎ የምዕራፍ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 25111 2 30 56 23 አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 የምዕራፍ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት፡፡

 

የምዕራፍ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት

Save Tender