Tender Detail

Tender Details

  • Company የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
  • Address ቤቴል አደባባይ ዝቅ ብሎ ፖስታ ቤት ፊለ ፊት ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0113696984
  • Website
  • Deadline01 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price400.00
  • Bid Securityለጽዳት እቃዎች 17,600.00 ብር ፣ ለደንብ ልብስ 10,000.00 ብር እና ለፈርኒቸር እቃ 15,000.00 ብር
  • opening date2026-01-01 00:00:00
  • Categories Furniture And Furnishing , Textile, Garment & Leather , Stationery Materials

የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የሚከተሉት እቃዎችና አገልግሎቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 02/2018

 

የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የሚከተሉት እቃዎችና አገልግሎቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 4 የጽዳት እቃዎች ---------------- 17,600.00
  • ሎት 2 የደንብ ልብስ ------------------ 10,000.00
  • ሎት 3 የፈርኒቸር እቃ ---------------- 15,000.00

በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋበዛሉ።

  1. በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤
  2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ቤተል ፖስታ ቤት አካባቢ በሚገኘው ወረዳ 06 ፋይናንስ ጽ/ቤት አንደኛ ፎቅ ባለው ቢሮ በመገኘት የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ ብር) በመክፈል ጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
  3. ከሎት1-ሎት 3 ላሉት እቃዎች ላቀረቡት ጠቅላላ የጨረታ ማስከበሪያ ሎቶች ፊት ባለው ዋጋ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም CPO በማዘጋጀት ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር የታሸገ እና በማህተም የተመታ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው፤
  4. ተጫራቾች ለአንድ እቃ አንድ ዋጋ ብቻ ማቅረብ አለባቸው፤
  5. ተጫራቾች የተጠቀሱትን እቃዎች በሙሉ ወይም በከፊል ማጫረት ይቻላል።
  6. የጨረታ ሰነዱን ማቅረቢያ የመጨረሻው ቀን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ድረስ ሆኖ በ11ኛ ቀን 3፡30 ሰዓት ላይ ይታሸጋል 4፡00 ሰዓት ተጫራች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳ 06 ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ይሆናል። ሆኖም አስራ አንደኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፤
  7. አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም
  8. ጽ/ቤት የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
  9. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን እቃዎች ናሙና በሙሉ በየሎቱ ከጨረታው ጋር ማስገባት አለባቸው፤
  10. ተጫራቾች የወሰዱትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን መቀየር አይችሉም።
  11. ተጫራቾች በጥቃቅን የተደራጁ ከሆነ ከአደራጃቸው ተቋም ሰነድ የሚወስዱበትና የውል ዋስትና ደብዳቤ ማፃፍ አለባቸው።

 

አድራሻ:- ቤቴል አደባባይ ዝቅ ብሎ ፖስታ ቤት ፊለ ፊት ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

ለተጨማሪ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 0113696984/0113697912

 

የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender