Tender Detail

Tender Details

  • Company የደብረብርሃን አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
  • Address ደብረብርሃን ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116813390
  • Website
  • Deadline02 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security20,000 /ሃያ ሺህ ብር ብቻ/
  • opening date2026-01-02 00:00:00
  • Categories Health Related Services , Health Care, Medical Industry Materials And Machinery

የደብረብርሃን አጠቃላይ ስፔሻላይዘድ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ የህሙማን ኦክስጅን ሲሊንደር ሙሌት ከነመጓጓዥያ ትራንስፖርት እንዲሁም የሲልደር ጥገና ለተከታታይ አንድ ዓመት የሚቆይ ግዥ አቅርቦት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የደብረብርሃን አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል


 

በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የደብረብርሃን አጠቃላይ ስፔሻላይዘድ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ የህሙማን ኦክስጅን ሲሊንደር ሙሌት ከነመጓጓዥያ ትራንስፖርት እንዲሁም የሲልደር ጥገና ለተከታታይ አንድ ዓመት የሚቆይ ግዥ አቅርቦት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት፡-

  • በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር እንዲሁም የህሙማን ኦክስጅን አምራችና አቅራቢ የብቃት ማረጋገጪያ የምስክር ወረቀት ያላቸው ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾች መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከሆስፒታሉ ገንዘብ ቤት መግዛት ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ኦሪጅናሉንና ኮፒ በጥንቃቄ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፣
  • ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የህሙማን ኦክስጅን ሲሊንደር ሙሌት ከነ መጓጓዥያ ትራንስፖርት እንዲሁም የሲልደር ጥገና አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  • ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን የህሙማን አክስጅን ሲሊንደር ሙሌት ከነ መጓጓዥያ ትራንስፖርት እንዲሁም የሲልደር ጥገና በሆስፒታሉ የጨረታ ሰነድ አይነትና ዝርዝር /ስፔስፊኬሽን/ መሰረት ማቅረብ አለባቸው።
  • ተጫራቾች ያሸነፉበትን የህሙማን ኦክስጅን ሲሊንደር ሙሌት ከነ መጓጓዥያ ትራንስፖርት እንዲሁም የሲልደር ጥገና ሙሉ በሙሉ በራሳቸው ትራንስፖርት ሆስፒታሉ ድረስ በተፈለገ ጊዜ ወዲያውኑ በማቅረብ ማስረከብ አለባቸው፡፡
  • ተጫራቾች ያሸነፉበትን የህሙማን ኦክስጅን ሲሊንደር ሙሌት ከነ መጓጓዥያ ትራንስፖርት እንዲሁም የሲልደር ጥገና ውለታው እስካልተቋረጠ ድረስ ዓመቱን ሙሉ ሲታዘዙ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
  • ተጫራቾች ሆስፒታሉ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ዋጋ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ይህ ማለት በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ ማቅረብ አይችሉም።
  • ተጫራቾች ሙሉ በሙሉ ዋጋ ማቅረብ አለባቸው። ዋጋ ነጣጥሎ መሙላት ከጨረታ ውድድር ውጭ ያስደርጋል፡፡
  • ተጫራቾች ሆስፒታሉ የህሙማን አክስጅን ሲሊንደር ሙሌት ከነ መጓጓዥያ ትራንስፖርት እንዲሁም የሲልደር ጥገና ባሸነፉበት ጥራትና ዋጋ ዝርዝር መሠረት ልዩነት ቢኖረውና የጥራት ችግር ቢከሰት በራሳቸውዉ ወጪ እንደገና የመተካት ግዴታ አለባቸው።
  • ተጫራቾች ያሸነፉትን የህሙማን ኦክስጅን ሲሊንደር ሙሌት ከነ መጓጓዥያ ትራንስፖርት እንዲሁም የሲልደር ጥገና ትክክለኛነቱን ሆስፒታሉ በሚመለከታቸው ባለሙያዎችና ሃላፊዎች በማረጋገጥ ይረከባል፡፡
  • ተጫራቾች ያሸነፉትን የህሙማን ኦክስጅን ሲሊንደር ሙሌት ከነ መጓጓዥያ ትራንስፖርት እንዲሁም የሲልደር ጥገና አቅርቦት ደረጃውን የጠበቀ መሆን አለበት ፣ በአቅርቦቱ ላይ የመጠንና የጥራት መጓደል ቢኖር በራሳቸው ወጪ የማስተካከል ወይም የመተካት እና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
  • ተጫራቾች ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር ብቻ/ እና ካሸነፉ በኋላ ያሸነፉበትን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ በባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ሆስፒታሉ ገንዘብ ቤት ድረስ ቀርበው ማስያዝ አለባቸው።
  • ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀን ውስጥ የውል ማስከበሪያ የአሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ ሆስፒታሉ 10% በማሲያዝ በውልና ማስረጃ ውለታ በመፈፀም ማቅረብ አለባቸው።
  • ተጫራቾች ከአሸነፉ በኋላ ሚያሲዙት የጨረታ ውል ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ከሆነ የጊዜ ቆይታው 12 ወር መሆን አለበት፡፡
  • ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ቀናት አየር ላይ ቆይቶ 16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ማስገባት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሳጥኑ 4፡00 ይታሸጋል በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን በዓላት ቀን ከሆነ በቀጣይ ስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ይከፈታል፡፡
  • የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለ60 ቀን ፀንቶ ይቆያል፡፡
  • ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥ ፋ/ን/አስ/ደ/ቡድን ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት፣ በስልክ ቁጥር 0116813390 ወይም 0116376994 በፋክስ 011681008 ቁጥር በመላክ መጠየቅ ይቻላል፡፡
  • መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን በሙሉ የመሠረዝ መብቱ እንዲሁም ግዥውን በጥቅል ወይም በተናጠል የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ደብረብርሃን አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

Save Tender