Tender Detail

Tender Details

  • Company የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address አስኮ ከጨረታ አለፍ ብሎ ፖሊስ ጣቢያው ጀርባ 200 ሜትር ገባ ብሎ ቢሮ ቁጥር 305 ላይ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0118 27- 87-49
  • Website
  • Deadline30 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Security30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር/
  • opening date2025-12-31 00:00:00
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት በ2ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ የፅዳት እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥው መለያ ቁጥር  002/2018

 

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት 2ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ

1. የፅዳት እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች ያለውን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች መወዳደር ትችላላችሁ።

  1. በዘርፉ ህጋዊ የሆነ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው።
  2. ተጫራቾች በተጨማሪ ታክስ (VAT) ከፋይ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ።
  3. በገንዘብ ሚኒስቴር ወይም በአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
  4. ተጫራቾች ለሚጫረቱት እቃዎች በሙሉ ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል እንዲሁም አንድ ናሙና ላይ ሁለት እቃ ማቅረብ ከውድድር ውጪ ያደርጋል። ናሙናዎችን እስከ 6 ወር ድረስ መልሰው ካልወሰዱ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
  5. አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ማቅረብ አይቻልም አንዱ በአንዱ ዋጋ ላይ ተነስቶ ማቅረብ አይቻልም።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከታች በሰንጠረዡ እንደተዘረዘረው በእያንዳንዱ ሎት ለየብቻ መሰረት በስሙ የተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ /CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው። (CPO) ከኦርጅናል ሰነድ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት፡፡

 

ሎት ቁጥር

የሎት ዝርዝር

የተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በኢትዮጵያ ብር

ምርመራ

ሎት 1

የጽዳት እቃዎች

30,000.00

የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ በባንኩ ባለስልጣናት መፈረሙ ተረጋግጦ ከሰነዶች ጋር መያያዝ አለበት

 

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ በመንግስት የስራ ሰዓት ለእያንዳንዱ የጨረታ ዓይነቶች በሎት የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ዋጋ 500 /አምስት መቶ የኢትዮጵያ ብር/ በመክፈል በጉ/ክ/ከተማ ወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት ግ/አስ/ደ/የሥራ ሂደት የቢሮ ቁጥር 305 በመቅረብ መውሰድ ይቻላል።

  1. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ልዩ አስተያየት የሚደረግላቸው እራሳቸው አምርተው ለገበያ በሚቀርብበት ዕቃ/ምርት/ ካልሆነ በስተቀር የተዘጋጀ ምርት/ዕቃ/ ከገበያ ላይ ገዝተው የሚወዳደሩ እንደማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ እና የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
  2. ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆኑን ወይም አለመሆኑን መጠቀስ አለበት ያልተጠቀሰ ከሆነ ቫት እንዳካተተ ይወሰዳል።
  3. ጽ/ቤቱ የሚገዛቸውን እቃዎች ከውል በፊት የእቃውን ብዛት 20% መጨመርም ሆነ መቀነስ ይችላል።
  4. ተጫራቾች ባሸነፉት አጠቃላይ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  5. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፏቸውን እቃዎች በውላቸው መሰረት ሙሉ ለሙሉ በራሳቸው ትራንስፖርት ጽ/ቤቱ ድረስ ገቢ የማድረግ ግዴታ አለባቸው።
  6. ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነዶችንና የዋጋ ማቅረቢያዎትን ፋይናንሻል ሰነዶች በተለያየ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ መቅረብ ይኖርበታል። ማንኛውም ተጫራች የሚያስገባው ሰነድ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጅናል እንድ ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ ማህተም በመምታት የሚጫረትበትን ዕቃ አይነት በትክክል በመፃፍ እንዲሁም በፖስታው ላይ ማህተም በመምታት ማስገባት ያለበት ሲሆን ስርዝ ድልዝ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ ዋጋ ያልሞላበት ዝርዝር እና አንድ እቃ ላይ ሁለት ዋጋ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እናሳውቃለን።
  7. በስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ የተደራጁ ማስረጃ በማቅረብ የሚወዳደሩ ድርጅቶች የጨረታ ሰነድ ብቻ በነፃ የሚሰጥ ሲሆን ከላይ ለተዘረዘሩት የጨረታ ሎቶች ሲፒኦ ያላቀረቡ ተጫራቾች ከውድድር ውጭ ይሆናሉ።
  8. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 305 ድረስ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ።
  9. ጨረታው በ10ኛው ቀን 10:30 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጉ/ክ/ከ/ወ/5 ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 305 የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል።
  10. አሸናፊ ተጫራች አሸናፊነታቸው በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ከ5 የቅሬታ ቀናት በኋላ በ10 ቀናት ውስጥ ውል መዋዋል አለባቸው።
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
  12. በጨረታ ማስታወቂያ ላይ ያልተገለጹ ካሉ በግዥ መመሪያ መሠረት ተፈፃሚ ይሆናሉ።

 

አድራሻ፡- ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት አስኮ ከጨረታ አለፍ ብሎ ፖሊስ ጣቢያው ጀርባ 200 ሜትር ገባ ብሎ ቢሮ ቁጥር 305 ላይ ይገኛል።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0118 27- 87-49 / 0118-27-86-62

 

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender