ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
Berhanena selam printing enterprise (ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት)
የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 007/18
ድርጅታችን ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡-
በጨረታ አንድ (ሎት 1):- የተለያዩ ተሽከርካሪዎች ግዥ፤
|
ተ.ቁ |
አይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
|
1 |
ከ38-60 ሰው የመጫን አቅም ያለው አውቶብስ (ባስ) |
በቁጥር |
1 |
|
2 |
ሚኒ ባስ |
በቁጥር |
1 |
በጨረታ ሁለት (ሎት 2)፡- የተለያዩ የቢሮ መገልገያዎች (ፈርኒቸሮች) ግዥ፤
|
ተ.ቁ |
አይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
|
1 |
ጠረጴዛ (የተለያየ አይነት እና መጠን ያላቸው) |
በቁጥር |
8 |
|
2 |
ወንበር |
በቁጥር |
59 |
|
3 |
ሼልፍ |
በቁጥር |
10 |
|
4 |
የልብስ ሳጥን (ቦክስ ሎከር) |
በቁጥር |
6 |
|
5 |
ባለ አራት መሳቢያ የብረት ፋይል ካቢኔት |
በቁጥር |
1 |
በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም ወቅታዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የገንዘብ ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ምዝገባ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅቱ ዋና መ/ቤት (አራት ኪሎ) አዲስ ህንፃ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የዕለት ገንዘብ ተቀባይ የማይመለስ ብር 300.00 ከፍለው በመግዛት ፋይናንሺያል የቴክኒካል የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውን እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ ነባሩ ህንፃ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሎት አንድ ለቀረበው ብር 50,000፣ በሎት ሁለት ለቀረበው ብር 30,000 በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው።
ጨረታው 5/5/ ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰአት ተዘግቶ በዕለቱ የቴክኒካል መጫረቻ ሰነድ (ከላይ የተገለፁ ለቅድመ ግምገማ የሚያገለግሉ ዶክመንቶች፣ የጨረታ ማስከበሪያ) ብቻ ከሰዓት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ነባሩ ህንፃ 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይረክቶሬት ቢሮ ይከፈታል። የፋይናንሽያል የመጫረቻ ሠነዶች የሚከፈቱት ቴክኒካል ተቀባይነት ላገኙት ብቻ ነው።
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።
ስልክ ቁጥር 011-1-55-52-30
ድረ-ገፅ (www.ethbspe.org)
Berhanena Selam printing enterprise አዲስ አበባ
ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት
