Tender Detail

Tender Details


ሀዋሳ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለ2018 ዓ/ም ትምህርት ዘመን ለትምህርት ሥራ ማስፈፀሚያ የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Hawassa College of Teacher Education (ሀዋሳ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ)


የጨረታ ማስታወቂያ

ሀዋሳ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለ2018 ዓ/ም ትምህርት ዘመን ለትምህርት ሥራ ማስፈፀሚያ የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን፡-

1. የሰራተኞች የደንብ ልብስ

2. ቋሚና አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን

3. የጽሕፈት መሳሪያዎችን

4. የጽዳት ዕቃዎችን

5. የስፖርት ትጥቆችን

6. የሕንፃ መሳሪያዎችን እና የቧንቧ ዕቃዎች

7. የኤሌክትሪክ ዕቃዎች

8. ኤሌከትሮኒክስና የኔትወርከ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በዘርፉ ለመጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች፡

1. በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን የሀገር ውስጥ ገቢ የከፈሉ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸውና የተጨማሪ እሴት ታከስ/ቫት/ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡

2. ተጫራቾች የኢ.ፌ.ድ.ሪ የገንዘብ ሚኒስተር ባዘጋጀው የአቅራቢነት ሊስት የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 16 ተከታታይየሥራ ቀናት ውስጥ የተዘጋጀውን የጨረታ ዶከመንት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/በኮሌጁ አካውንት 1000013492496 ገቢ በማድረግ በመከፈል ዘወትር በሥራ ቀናት በኮሌጁ ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬከቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ ከኮሌጁ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልተው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 16ኛው የሥራ ቀን ድረስ በቢሮ ቁጥር 14 ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

5. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ በ6፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ይከፈታል፡፡

6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ የድርጅታቸውን ማህተም ማድረግና በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

7.ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ቼከ /CPO/ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

8. ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስልክ ቁጥር 0462216946/0462210487

ሀዋሳ መምህራን ትምህርት

 ኮሌጅ

Save Tender