በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለቂልጦ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ኮሚኒቲ ፋርማሲ ብቁ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡
የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለቂልጦ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ኮሚኒቲ ፋርማሲ ብቁ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስለግንባታው የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ በማይመለስ ብር 350(ሶስት መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል በምስ/አዘ/በር/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 19 ድረስ በመምጣት ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነድ መግዛት ትችላላችሁ።
በዚህ ጨረታ ስሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች GC/BC6 እና ከዚያ በላይ የሆኑ
- ተጫራቾች በዘርፉ ያላቸው የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ወቅታዊ የግብር ክፍያ ማረጋገጫ የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ፤ በአቅራቢዎች ስም ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው የሚገልጽ ማስረጃና ሌሎች ሰነዶችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 80,000 (ሰማንያ ሺህ) ብር በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በCPO በምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም አሰርተው ለዚህ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በታሸገ ፖስታ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል የጨረታ ሰነድ ማስገባት አለባቸው። ዘግይቶ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ተጫራቾች የቴከኒካል እና ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዶችን ለእያንዳንዳቸው አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ የጨረታ ሰነድ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ ህጋዊ ማህተም በማድረግ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ21 ተከታታይ የስራ ቀናት ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ21 ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ይከፈታል፡፡
- የግንባታው ሳይት (ቦታ) በምስ/አዘ/በ/ወረዳ በቂልጦ 01 ውስጥ ነው።
- በተጫራቾች ተሞልተው የሚቀርቡ ፋይናንሻል ዋጋዎች እና የግንባታ ስራው ቴክኒካል የማወዳደሪያ ሀሳብ ደጋፊ ሰነዶች በግልጽና በጥራት የሚታዩና ስርዝ ወይም ድልዝ ያልሆኑ መሆን አለባቸው፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የወረዳው ከተማ(ቂልጦ) ከአዲስ አበባ ርቀቱ 221 ኪሎ ሜትር ሲሆን 176 ኪሎ ሜትር አስፓልት እና 45 ኪሎ ሜትር ፒስታ መንገድ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 09 27 17 59 14 /09 33 62 02 20
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የምስራቅአዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቂልጦ
