Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ከተማ የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎችና አገልግሎቶች በሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ንፋስ ስልክ ላፍቶ /ቅ/ጽ/ቤት


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር አሽ/ተሽ/ፍ/ቁ/ባ/ን/ላ/ቅ/ጽ/ቤት01/2018

 

በአዲስ አበባ ከተማ የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎችና አገልግሎቶች በሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  • ሎት1:- የሠራተኞች ደንብ ልብስ
  • ሎት2፡- አላቂ የፅህፈት ቤት ዕቃዎች
  • ሎት3፡- የፅዳት ዕቃዎች
  • ሎት4፡- የመኪና ጌጣጌጥ
  • ሎት5:- ህትመት ሥራዎች

በዚሁ መሰረት በዘርፉ የተሰማራችሁ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለጹትን በማሟላት መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1. ተወዳዳሪዎች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፣የግብር ከፋይመለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅ/ጽ/ቤቱ ድረስ ቀርባችሁ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል ከ/ቅ/ጽ/ቤት ከፋይናንስ ቡድን ቢሮ መውሰድ ትችላላችሁ።
  3. በሎት 1፡2፣3፣4 ናሙና ማቅረብ ግዴታ ያለባቸው ሲሆን ናሙና ባልታየባቸው ዕቃዎች መወዳደር አይቻልም።
  4. ተጫራቾች የመጫረቻ የሰነድ የዋጋ ማወዳደሪያ ኦርጅናል እና የሰነድ ኮፒ እና የፋይናሽያል ኮፒ በአንድ ላይ በድምሩ በ3 ፖስታ በማሸግ በመለየት መቅረብ አለባቸው። የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒአ በቴክኒካል ፖስታ ውስጥ አብሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስለጣን ንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅ/ጽ/ቤት በሚል ስም በባንከ በተመሰከረለት ሲፒኦ፣ መመሪያው በሚፈቅደው መሠረት ጨረታው ከመክፈቱ በፊት ማስያዝ አለበት፡፡
  6. ለሁሉም ሎቶች የጨረታው አሸናፈ ያሸነፈበትን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት ቅ/ጽ/ቤቱ ድረስ ያቀርባል።
  7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ብቻ በግልጽ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመሙላት በግርጌው ስም፣ ፊርማ በማኖር በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር የምትችሉ ሲሆን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅ/ጽ/ቤቱ የሚከፈት መሆኑን እየገለጽን ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

 

አድራሻ፡- ለቡ መብራት ሃይል አደባባዩን ከፍ ብሎ አርሴማ ቤተክርስቲያን አጠገብ አሽ/ተሽ/ንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

ለበለጠ መረጃ ስልክ፡- 0913926358/0920094528/

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ንፋስ ስልክ ላፍቶ /ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender