Tender Detail

Tender Details


በየካ ክ/ከ የኮሪያ ዘማቶች መታሰቢያ ጤና ጣቢያ በ2018 በጀት አመት በመንግስት ከተመደበለት ትሪዠሪና የውስጥ ገቢ መደበኛ በጀት ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን በሀገር አቀፍ ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በየካ ክ/ከተማ የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ ጤና ጣቢያ


 

ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በየካ ክ/ከ የኮሪያ ዘማቶች መታሰቢያ ጤና ጣቢያ በ2018 በጀት አመት በመንግስት ከተመደበለት ትሪዠሪና የውስጥ ገቢ መደበኛ በጀት ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን በሀገር አቀፍ ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  • ሎት-1- መድሀኒት፣ የላብራቶሪ ሪኤጀንትና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች
  • ሎት-2- የጽዳት ዕቃዎች

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች -

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የአቅራቢነት ፈቃድ መረጃ፣ የቲን (TIN) እና የቫት (VAT) ተመዝጋቢ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. አሸናፊ ተጫራች ድርጅቶች ውል ለመውሰድ በቅድሚያ በጨረታ ያሸነፉበትን ጠ/ዋጋ 10% ውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ በእያንዳንዱ ሎት ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከተቋሙ ፋይናንስ ክፍል 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 302 በመውሰድ እና የጨረታ ሰነዱ ላይ የሚጫረቱበትን ዋጋ በመሙላት እና ስም፣ ፊርማና የድርጅቱን ህጋዊ ማህተብ በማድረግ አርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኢንቨሎፕ በመ/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /CPO/

 

ሎት

1

2

ብር

20,000.00

10,000.00

 

  1. ጨረታው የሚከፈተው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነድ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን በዚህ ቀን 3፡30 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በይፋ ይከፈታል።
  2. የአገልግሎት ጊዜ ለሚጠይቁ ዕቃዎች በትንሹ ከአንድ አመት በላይ እና በግልጽ የሚታይ መሆን አለበት ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ፡- ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል ጀርባ፣ የካ ክ/ከ ወረዳ 4 አስተዳደር ጽ/ቤት ጎን

ለበለጠ መረጃ ስ.ቁ፡- 0111-220-624/0350

 

በየካ ክ/ከ የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ ጤና ጣቢያ

Save Tender