Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
  • Address ደብረ ማርቆስ ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0587713052
  • Websitehttps://www.era.gov.et
  • Deadline28 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Securityጠቅላላ ዋጋ 2% (ሁለት በመቶ)
  • opening date2025-12-29 00:00:00
  • Categories Wood And Wood Working , Forest And Tree Sales

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት በቡሬ ሴክሸን ላይ ተክሎ ያሳደጋቸውን ባህር ዛፍ እና የተለያዩ ዛፎች ብዛት 136 ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት


 

የዛፍ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር ጨ-01/2018

 

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት በቡሬ ሴክሸን ላይ ተክሎ ያሳደጋቸውን ባህር ዛፍ እና የተለያዩ ዛፎች ብዛት 136 ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም የታደሠ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈላችሁ ተጫራቾች አስፈላጊውን ማስረጃ በማያያዝ በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን ዛፎቹን በቦታው በአካል በመገኘት ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከ2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

  1. ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% (ሁለት በመቶ) ያላነሰ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ዋና (Original እና ኮፒ (Copy) ሠነዱን ለየብቻው አሽጐ በአንድ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት በዲስትሪክቱ ግዥ አቅርቦትና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ በመቅረብ ሰነዱን በመውሰድና በጥንቃቄ በመሙላት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
  3. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ታሽጐ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ሆኖም ቀኑ በበዓል ወይም በእሁድ ምክንያት ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  4. የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ወይም ሲፒኦ (CPO) ለተሸናፊዎች ከአምስት ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ይመለሳል።
  5. የጨረታው አሸናፊ በፅሑፍ እንደገለፁለት በአካል ቀርቦ ውል መፈፀም አለበት። ይህን ባይፈፅም ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ተወርሶ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
  6. የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በኢ.መ.አ ንግድ ባንክ አካውንት (ERA D/M/R/M/D Account No. 1000322269165) በመክፈል መግዛት ይቻላል። አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ገንዘብ ክፍያ በመፈፀም ንብረቱን ማንሳት ይኖርበታል።
  7. ዲስትሪክቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0587713052 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

 

ደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት

Save Tender