Tender Detail

Tender Details


የአማራ ክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ደሴ ቅርንጫፍ በ2018 በጀት ዓመት ለተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አቅርቦቶችን ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ካላቸው አቅራቢዎች በሎት አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የአማራ ክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ደሴ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የአማራ ክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ደሴ ቅርንጫፍ በ2018 በጀት ዓመት ለተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አቅርቦቶችን ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ካላቸው አቅራቢዎች በሎት አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ሎት 1 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች

ሎት 2 የፅህፈት መሳሪያዎች

ሎት 3 የፅዳት እቃዎች

ሎት 4 የመኪና መለዋወጫ እቃዎች

ሎት 5 የህክምና ላቦራቶሪ ሪኤጀንቶች

ሎት 6 ላቦራቶሪ የህክምና መሳሪያዎች

ሎት 7 የመኪና ጎማዎች

ሎት 8 ኤሌክትሪክ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል።

  1. በየዘርፉ አግባብነት ያለው በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር Tin Number/ ማቅረብ የሚችል
  2. የግዥ መጠን ብር 200,000(ሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት/ ተመዝጋቢነት የሚገልፅ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
  3. ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-2 የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራቾች የዕቃዎችን ዝርዝርና ስፔስፍኬሽን ወይም ዝርዝር መገለጫ ጨረታ ሰነዱ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር /በመክፈል በኢንስቲትዩቱ ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 3 የጨረታ ሰነድ በመግዛት መሳተፍ ይቻላል።
  4. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መገለጫ ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማገኘት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ የሚሸጥበትን ዋጋ በትክክል በመሙላት በጠቅላላ ከሞሉት ዋጋ ላይ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በማሰብ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ መሂ 1 በመቁረጥ ከጨረታ ፖስታው ጋር አሽገው ማቅረብ አለባቸው።
  6. ተጫራቾች የሞሉትን የጨረታ ሰነድ ኦርጅናል ሰነድ እና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻው በመለየት በታሸገ ፖስታ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን ከጧቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ አማራ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ደሴ ቅርንጫፍ የግዥ ቡድን ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርበታል።
  7. በጨረታ ሰነዱ ላይ ግልፅ ያልሆኑ ጉዳዮች ካሉ ማብራሪያ ለመጠየቅ በስልክ ቁጥር፡- 033 311 5220 ወይም በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ። ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን ከጧቱ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ላይ ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙቡት በአማራ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ደሴ ቅርንጫፍ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
  8. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የህዝባዊ በዓል ቅዳሜ እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት እና ቦታ የሚከፈት ይሆናል።
  9. ጨረታውን አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት በሚያቀርበው ቋሚ እቃዎች ላይ የ6 ወር ጋራንቲ መስጠት ይጠበቅባቸዋል።
  10. የጨረታው አሸናፊ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ በማቅረብ በሚመለከተው ባለሙያ እየተረጋገጠ በመ/ቤቱ ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይጠበቅበታል።
  11. በመጫረቻ ሰነድ ላይ ከሰፈሩት የውል ቃሎችና ሁኔታዎች ጋር መሰረታዊ ልዩነት ያለው ሀሳብ ማቅረብ ከጨረታው ተሳታፊነት ያሰርዛል።
  12. ኢንስቲትዩቱ ጨረታ አሸናፊ ከለየ በኋላ እንደ ተቋሙ በጀት መ/ቤቱ የሚገዛውን የእቃ ብዛት 20 በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብት ይኖረዋል።
  13. ከጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው ያንዱ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ከእነቫቱ በመሙላት የድርጅቱን ማህተም ፊርማ አድራሻ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል። በነጠላ ዋጋ ላይ ሆን ተብሎ የተጋነነ ስርዝ ድልዝ ከጨረታ ተሳታፊነት ያሰርዛል።
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። የተጫራቾች መመሪያን ሳይገነጠል አያይዘው ማቅረብ ግዴታ ነው።
  15. ሳምፕል የፅዳት የጽህፈት መሳሪያዎች በቀረበው ሳምፕል መሰረት መሙላት ይጠበቅባቸዋል።
  16. የጨረታ አሸናፊዎች የሚለዩት በሎት በመሆኑ የገዙትን ሰነድ ሙሉ ለሙሉ መሞላት ይኖርበታል ከፍት ያልተሞላ ዋጋ ካለ ከውድድር ውጭ ይደረጋል።

 

የአማራ ክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ደሴ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

Save Tender