በማ/ኢ/ክ/መ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ቢሮ በሀላባ ዞን የሀላባ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጁ በ2018 በጀት ዓመት ለኮሌጅ የስልጠና መስኮችና ለኮሌጁ የስራ እንቅስቃሴ የሚሆኑ ደረጃቸውን የጠበቁ ግብአቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በማ/ኢ/ክ/መ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ቢሮ
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 001/2018
በማ/ኢ/ክ/መ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ቢሮ በሀላባ ዞን የሀላባ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጁ በ2018 በጀት ዓመት ለኮሌጅ የስልጠና መስኮችና ለኮሌጁ የስራ እንቅስቃሴ የሚሆኑ ደረጃቸውን የጠበቁ ግብአቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም መወዳደር የምትፈልጉ፡-
- ተጫሪቾች በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና ከሀገር ውስጥ ገቢባለ ስልጣን የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- በዚህም መሰረት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 ተከታታይ የሥራ ቀናት የሀላባ ፖሊ ቴክኒክ ቢሮ ቁጥር 23 /ሃያ ሶስት/ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተገጋገጠ ብር 2,000 (ሁለት ሺህ ብር) ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 ተከታታይ የሥራ ቀን የሀላባ ፖሊ ቴክኒክ ቢሮ ቁጥር 23 /ሃያ ሶስት/ በመቅረብ የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ፖስታ በማድረግና እያንዳንዱ ተጫራች ሙሉ አድራሻውን በግልጽ በሚታይ ሁኔታ በመጻፍ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገቢየሚደረግ ጨረታ ማስታወቂያ ከታተመ ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ሃያ ተከታታይ የሥራ ቀናቶች ውስጥ ሲሆን በ20ኛው ቀን 1፡30 ሰዓት ተዘግቶ በ21ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰእት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሀላባ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በሮ ቁጥር 4 ላይ ይከፈታል፡፡ የጨረታ መዝጊያ መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ተዘግቶ ይከፈታል።
- የጨረታ ሰነዱን ለማዛባት የሚሞከሩ ያለበቂ ምክንያት ውል ለማይገቡና ውል ለሚያፈርሱ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ ከመሆናቸው በተጨማሪ ለወደፊትም በመንግስት ግዥ እንዳይሳተፉ ይደረጋል፡፡ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለመንግስት ውርስ ይደረጋል፡፡
- አሸናፊው እንዲታወቅ ያስያዙትን ገንዘብ ለተሸናፊዎች ወዲያውኑ የሚመለስ ይሆናል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበርያ በአሸናፊው ጠቅላላ ዋጋ ቢድ ቦንድ 10 በመቶ ያስይዛል፡፡
- ተወዳዳሪዎች ራሳቸውን ከጨረታ ማግለል ቢፈልጉ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማመልከቻ መጻፍ እና ጨረታ ሳጥኑ ውስጥ በማስገባት ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል ይችላሉ፡፡
- ተወዳዳሪዎች ኮሌጁ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በተጨማሪም ጨረታውን ያሸነፈው ተጫራች ድርጅት ዕቃውን ኮሌጅ ያለበት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
ለጨረታው የተዘጋጁ ሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፡፡
ሎት 1ኛ በአውቶሞቲቪ
ሎት 2ኛ በማምረቻ ዘርፍ
ሎት 3ኛ በእስቴሽነሪ
ሎት 4ኛ በአይ ሲ ቲ ዘርፍ
ሎት 5ኛ በግንባታ ዘርፍ
ሎት 6ኛ በኤሌክትሮኒክስ ዘርፍ
ሎት 7ኛ አሽከርካሪ በመንጃ ፍቃድ ማሰልጠኛ ማዕከል
በማ/ኢ/ክ/መ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ቢሮ
