Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara Forest Enterprise (የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ)
  • Address ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 አዲሱ መናኸሪያ ጀርባ እንስሳት ህክምናና ላብራቶሪ ግቢ ውስጥ አማራ ደን ኢንትርፕራይዝ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 13 ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058 226 3095
  • Websitehttps://amharaforest.gov.et
  • Deadline21 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security2%
  • opening date2025-12-21 00:00:00
  • Categories Wood And Wood Working

በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት የቁም ደንና የጣውላ ምርት ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Amhara Forest Enterprise (የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ)


ጨረታ ማስታወቂያ

የቁም ደንና የጣውላ ምርት ሽያጭ

 

በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት ደ/ጎንደር ዞን ጉና በጌምድር ወረዳ አርጋ ድድም ቀበሌ አንጨትና ዋልጋሜዳ የመንግስት ደን ውስጥ 15,715,8oሜ/ኩብ ነጭ ባህርዛፍ፣ 4,047.73ሜ/ኩብ የፈ/ፅድ በድምሩ 19,763.53 ሜ/ኩብ ቁም ደን፣ አዊ ዞን ባንጃ ወረዳ በአረፅ ቀበሌ በተርያ የመንግስት ደን ውስጥ የሚገኘውን 5,757.62 ሜ/ኩብ የፈ/ጽድ ቁም ደን፣ በደ/ማርቆስ እንጨት መሰንጠቂያ ማሽን የተመረተ 180.6687 ሜ/ኩብ የፈ/ጽድ ጣውላ ምርትና በደ/ታቦር እንጨት መሰንጠቂያ ማሽን የተመረተ 87.14 ሜ/ኩብ የፈ/ጽድ ጣውላ ምርት ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች፦

    1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርቲፍኬት ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
    2. የሽያጩ መጠን 200,000.00/ሁለት መቶ ሺህ /ብር በላይ ከሆነ የተእታ /VAT/ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
    3. ለጨረታ የቀረቡትን ጣውላና ቁም ደን ምርቶች ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች የዘወትር በሥራ ሰዓት በቦታው ተገኝተው ማየት ይችላሉ።
    4. የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ /ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ/ በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት ባሕርዳር ቀበሌ 14 አዲሱ መናኸሪያ ጀርባ እንስሳት ማዳቀያ ግቢ ዉስጥ ከኢንተርፕራይዙ ቢሮ ቁጥር 06 እና በሁሉም ቅ/ጽ/ቤቶች የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
    5. ተጫራቾች ለመግዛት የሚፈልጉትን ምርት ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ/CPO/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
    6. ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን ጣውላና ቁም ደን ምርቶች/ በኦሪጅናል ዋጋ መሙያ ቅጽ የሚገዙበትን ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ስምና አድራሻቸውን በመፃፍ ፈርመው በመሙያው ሰነዱ ላይ ማህተም በማስቀመጥ የታሸገውን የጨረታ ፖስታ በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06፣ ደ/ብርሃንና ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ‹‹ቁም ደን እና የጣውላ ምርት የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ›› ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ (ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ) እስከ 10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ሳጥኑ ታሽጎ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ይሁን እንጅ ተጫራቾች ባይገኙም ይከፈታል።
    7. ተጫራቾች የሚሞሉት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ 15% ተእታን አይጨምርም። ሆኖም አሸናፊው ባሸነፈበት ዋጋ ላይ 15% ተእታን ጨምሮ ይከፍላል።
    8. ተጫራቾች ጣውላና ደኑን በተመለከተ ቅልቅል ደንና ሎት ተብሎ ተብሎ የቀረበውን ሁሉንም ክፍልፋይ ሎት/ መሙላት ይጠበቅባቸዋል።
    9. በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
    10. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
    11. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥርባ/ዳር 058 226 3095፣ ደ/ታቦር 058 441 0306፣ ደ/ብርሃን 011 637 5017፣ እንጅባራ 058 227 0485፣ ደ/ማርቆስ 058 871 9004፣ ኮ/ቻ 09 14 71 66 36 ደውሎ መጠየቅ ይችላል።

 

የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት

Save Tender