ደቡብ ምዕራብ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የ2017 በጀት ዓመት የሂሳብ ሰነድ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስመርመር ወይም ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል።
SOUTHWEST CONSTRUCTION CORPORATION (የደቡብ ምዕራብ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን)
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሂሳብ ምርመራ ኦዲት ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የመ/ቤቱ ሥም : ደቡብ ምዕራብ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን (ደምኮኮ)
የጨረታ ቁጥር : 003/2018
ደቡብ ምዕራብ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የ2017 በጀት ዓመት የሂሳብ ሰነድ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስመርመር ወይም ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት:
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው፣
- የግብር ከፋይነት መለያ ሠርቲፊኬት ያላቸው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ እና በጨረታ ለመሣተፍ ከገቢዎች ፍቃድ ያላቸው፣
- ከተለያዩ ተቋማት የሂሳብ ምርመራ /ኦዲት/ በማድረግ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ያላቸው /ማቅረብ የሚችሉ፣
- የጨረታ ሰነድ የሚሸጥበት ጊዜና ቦታ፦
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 /አሥራ አምስት/ ቀናት ድረስ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በኮርፖሬሽኑ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000615509209 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ የንግድ ፍቃዳቸውን ኮፒ ይዘው በመቅረብ በቦንጋ ከተማ 03 ቀበሌ አካባቢ ከሚገኘው ከተቋሙ የግዥና ንብረት አስተዳደር አገልግሎት ቢሮ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው የሚከፈትበት እና ሰነዱ የሚቀርብበት ጊዜ፦
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ ከ2፡30 እስከ 6፡30 እና ከቀኑ ከ7፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው በማግስቱ በ17ኛው ቀን ጠዋት 3፡30 ታሽገው 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- 17ኛው ቀን ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- በጨረታው አከፋፈት ሂደት የሚገኙ ህጋዊ ወኪሎች የውክልና ማረጋገጫ መያዝ ይጠበቅባችኋል።
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች አለመገኘት የጨረታውን አከፋፈት ሃደት አያስተጓጉልም።
- የጨረታ ዋስትና ፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታ ዋጋ ሁለት ከመቶ /2%/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ከ90 /ዘጠና/ ቀናት ወይም ሦስት ወር ያላነሰ ጊዜ ያለው የባንክ ዋስትና በባንኩ ዋና መ/ቤት የተረጋገጠው ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።
- የጨረታ ሠነድ አቀራረብ ሁኔታ፦
የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት የግብር ከፋይነት ሠርቲፊኬት እና የታክስ ክፍያ ማረጋገጫ ሰነዶች፣ በጨረታው ለመሳተፍ ከገቢዎች የተሰጠ ማስረጃ እና የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተደገፈ /CPO/ ከዋና ኦርጂናል/ የዋጋ ማቅረቢያ ጋር በአንድ ላይ ታሽገው ማቅረብ አለባቸው። ፋይናንሻል ዶክሜንት ዋና እና ኮፒ ለየብቻ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል።
ቴክኒካል ዶክመንት ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል።
የኮፒና ኦርጅናል መለያየት ካለ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ካላስያዙ ከጨረታ ውጪ ይሆናሉ፡፡
ባቀረቡት የዋጋ ማቅረቢያ እና የመጫረቻ ሰነድ ላይ እራስዎ ስለመሙላትዎ የድርጅቱ ሙሉ አድራሻ አንዲሁም ፊርማ እና ማህተም ማረጋገጥ ይኖርበታል።
ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የደቡብ ምዕራብ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
