የሰሜን ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ ግዥና ንብ/አስ/ር ቡድን የሰሜን ወሎ ዞን ጤና መምሪያ በግቢው ውስጥ ለሚያስገነባው የመሰብሰቢያ አዳራሽ የእጅ፣ የሙያ እና አጠቃላይ የማቴሪያል ዋጋን ጨምሮ ከደረጃ 6 እና በላይ ያላቸውን በBC/GC ሥራ ዘርፍ የተሰማሩትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
የሰሜን ወሎ ዞን ገ/ኢ/ል መምሪያ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ር ቡድን
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የሰሜን ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ ግዥና ንብ/አስ/ር ቡድን የሰሜን ወሎ ዞን ጤና መምሪያ በግቢው ውስጥ ለሚያስገነባው የመሰብሰቢያ አዳራሽ የእጅ፣ የሙያ እና አጠቃላይ የማቴሪያል ዋጋን ጨምሮ ከደረጃ 6 እና በላይ ያላቸውን በBC/GC ሥራ ዘርፍ የተሰማሩትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡-
- በግንባታ ሥራ ዘርፍ የተሰማሩና የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- ህጋዊ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin number/ ያላቸው
- ተጫራቾች ደረጃ 6 እና በላይ የሆኑ BC/GC ፈቃድ ያላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የመልካም ሥራ አፈጻጸም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ በCPO: በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ በመሂ/1 በመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ የተቆረጠ ደረሰኝ እና ከጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የተሰጠ የጨረታ ማስከበሪያ የዋስትና ደብዳቤ ከጨረታው አርጅናል ሰነድ ጋር የተወሰደው የገንዘብ መጠንን በማስጠቀስ በፖስታ ውስጥ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ማንኛውም ግብርና ታክስ አካቶ መሙላት አለባቸው
- ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው ባሉት ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርበው 10% ዋስትና በማስያዝ ውል መፈጸም አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱ ከ02/04/2018 እስከ 23/04/2018 ዓ.ም ድረስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር40 ድረስ በመምጣት ብር 500 /አምስት መቶ/ በመከፈል መግዛት ይኖርበታል ።
- ጨረታ በ23/04/2018 ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል። የማይገኝ ተጫራች በተገኙት ስምምነት ይከፈታል። ባይገኝም በህግ ተገዥ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በሁሉም የጨረታ ሰነዳቸው ላይ ክብ ማህተምና ፊርማ መፈረም ይኖርባቸዋል፡፡
- ውድድሩ በሎት ወይም በድምር ዋጋ ስለሆነ ሁሉም የግንባታ ሥራዎች ዋጋ መሞላት አለበት፡፡
- አሸናፊው አካል በፍትህ ውለታ መወሰድ /መያዝ/ ግዴታው መሆኑን ግንዛቤ መያዝ ይኖርበታል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- ቲን ነምበር፣ ንግድ ፈቃድ እና የቫት የምስክር ወረቀት ለየብቻ በአንድ ገጽ ኮፒ ተደርጎ መያያዝ አለበት
- የተሰጡን የጨረታ ሰነዶች ተሟልተው ሳጥን ውስጥ ከገቡ የመክፈቻ ጊዜውን ሳይጠብቅ ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታ መክፈቻው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር (0333311597/2680) ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የሰሜን ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ ግዥና ንብ/አስ/ር ቡድን
