የኢየሩሳሌም መታሰቢያ ድርጅት በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 የቤት ቁጥር 1030/79 የሚገኝ ሲሆን የመታሰቢያ ድርጅቱን የስብሰባ አዳራሽ የጥገና ስራዎች እና አዲስ የሰርቪስ ቤት በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ኢየሩሳሌም መታሰቢያ ድርጅት አዲስ አበባ
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢየሩሳሌም መታሰቢያ ድርጅት በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 የቤት ቁጥር 1030/79 የሚገኝ ሲሆን የመታሰቢያ ድርጅቱን የስብሰባ አዳራሽ የጥገና ስራዎች እና አዲስ የሰርቪስ ቤት በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
- ጥገና የሚደረግለት የስብሰባ አዳራሽ ቦሌ በሚገኘው ጽ/ቤታችን በመገኘት የሚጠገነውን አዳራሽ ማየት ይቻላል። የጨረታ ሰነዱን ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 02 የቤት ቁጥር 1030/79 በሚገኘው የኢየሩሳሌም መታሰቢያ ድርጅት ጽ/ቤት ቢሮ ከታህሳስ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በሥራ ቀናትና ሰዓት መውሰድ ይቻላል።
- ተጫራጮች የጨረታ ዋጋቸውን በተጠቀሱት ቀናት ጠዋት ከ2፡30 እስከ 6፡30 እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 እስከ 10፡30 ባለው ጊዜ ጨረታውን መግዛት ይችላሉ። ጨረታውን በሚያቀርቡበት ጊዜ ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በሲፒዩ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የሚዘጋበት ቀን፡- ታህሳስ 16/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00.
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን፡- ታህሳስ 16/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ቦሌ በሚገኘው የድርጅቱ ጽ/ቤት ነው።
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም በሌሉበት ይከፈታል።
- ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ዘግይቶ የመጣ የጨረታ ፖስታ ተቀባይነት የለውም።
- የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለጸበት በ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ስራውን መጀመር ይኖርበታል። በነዚሁ ቀናት ውስጥ ስራውን መጀመር ካልቻለ የጨረታ ማስከበሪያው ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0111 55 05 59 ወይም 0111 56 49 31 ደውሎ መረዳት ይቻላል።
ኢየሩሳሌም መታሰቢያ ድርጅት አዲስ አበባ
