Tender Detail

Tender Details


የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ኤሌክትሮኒከስ፣የቤት ማስዋቢያ፣ አልባሳት፣ ጫማ፣ የቤት ዕቃ፣ እስፔርፓርት፣ምግብነክ፣ኮንስትራክሽን፣ የዕዳት ዕቃ እና ልዩ ልዩ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ኤሌክትሮኒከስ፣የቤት ማስዋቢያ፣ አልባሳት፣ ጫማ፣ የቤት ዕቃ፣ እስፔርፓርት፣ምግብነክ፣ኮንስትራክሽን፣ የዕዳት ዕቃ እና ልዩ ልዩ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን እቃዎች 03/04/2018 ጀምሮ ሳምፕል በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገልፃል፡፡

ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች:-

1. በዘርፉ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ

2. ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ እቃዎቹን ለመግዛት የሚቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) (ሲ.ፒ.አ (C.P.O) ማቅረብ የሚችል፤

3. በግልፅ ጨረታ ቅ/ጽ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ በመሙላት በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤

4. ተጫራቹ በጨረታው እሸንፎ የገዛውን እቃዎች ከፍያውን በ05 ቀናት ውስጥ መፈፀም አለበት፤

5. እቃዎቹን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በ5 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ለመንግስት ገቢ ይሆናል፤

6. በጨረታው ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፤

7. አሳማኝ የሆነ ምከንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል፤

8. ማንኛውም ተጫራች እቃዎቹን ካሸነፈ በኋላ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈልግ እንደየቦታው ርቀት በቀነ ገደብ መሸኛ ሊሰጣቸው ይችላል፤

9. ተጫራቹ እቃዎችን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም፤

10. ተጫራቾች የሞሉትን የግልፅ ጨረታ ሰነድ ከ03/04/2018 ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በጅግጅጋ ጉ/ኮ/ቅ/ጽ/ቤት የእቃ አወጋገድ ቢሮ በመቅረብ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በ06/04/2017 3:45 ሰአት ተዘግቶ ከረፋዱ 4፡00 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፤

NB: አሸናፊ ተጨማሪ እሴት ታከስ (ቫት) 15% (አስራ አምስት ፐርሰት) የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ፤ ሳምፕል ሳያዩ የሚጫረቱ ተጫራቾች ቅ/ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም::

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት

Save Tender