የአማኑኤል ከተማ ወተት ልማትና ግብይት ህብረት ሥራ ማህበር አንድ ሲኖ ትራክ ካሶኒ መኪና፣ አንድ የወተት ማጓጓዣ ስቴንስ ስቲል ባለ 15,000 ሊትር ታንከርና አንድ የወተት ማጓጓዣ ካሶኒ ስኖትራክ መኪና ባለ 15,000 ሊትር ስቴንለስ ስቲል ቦቲ የተገጠመለት መኪና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የአማኑኤል ከተማ ወተት ልማትና ግብይት ህብረት ሥራ ማህበር
የጨረታ ማስታወቂያ
የአማኑኤል ከተማ ወተት ልማትና ግብይት ህብረት ሥራ ማህበር በአማራ ክልል በምስራቅ ጎጃም ዞን በማቻከል ወረዳ በአማኑኤል ከተማ በደንብና አዋጅ በ1998 ዓም የተቋቋመ ማህበር ነው ማህበሩ የወተት ምርት በመሰብሰብና እሴት በመጨመር ወተት እና የወተት ተዋጽኦ በማቅረብ እየሰራ ያለ ማህበር ነው። ማህበሩ አንድ ሲኖ ትራክ ካሶኒ መኪና፣ አንድ የወተት ማጓጓዣ ስቴንስ ስቲል ባለ 15,000 ሊትር ታንከርና አንድ የወተት ማጓጓዣ ካሶኒ ስኖትራክ መኪና ባለ 15,000 ሊትር ስቴንለስ ስቲል ቦቲ የተገጠመለት መኪና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ የንግድ ድርጅቶች፣ ማህበራት ወይም ኃ/የተ/የግ/ማህበር በጨረታው እንድትሳተፉ ማህበሩ ይጋብዛል።
-
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፣ ከመንግስት የሚጠበቅባቸውን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተቀበሉ መሆን አለባቸው።
-
- ስለ ታንከሩ ሞዴል፣ የተሰራበት አገር፣ የታንከሩ አቅም፣ የተመረተበት ዓ.ም እንዲሁም የአምራቹን ኩባንያ መረጃ ማቅረብ የሚችል የምትችል።
- ስለ መኪናው ሞዴል፣ የተሰራበት አገር፣ የመኪናው አቅም የተመረተበት ዓ.ም እንዲሁም የአምራቹን ኩባንያ መረጃ ማቅረብ የሚችል/የምትችል።
-
- ታንከሩን፣መኪናውንና መኪናውን ከነታንከሩ በተቀመጠው ዝርዝር ስፔስፊኬሽን መሰረት ማህበሩ በሚያቀርበው ባለሙያ አስመርምሮ ማስረከብ የሚችል የምትችል።
-
- በግብርና ግብዓት ሽያጭ፣ የግብርና ግብዓት አስመጪና ላኪ፣ ታንከር መገጣጠሚያ ወይም የወተት እና ወተት ተዋጽኦ ምርቶች መቀነባበሪያ ስፔር ፓርት ንግድ ፈቃድ ያለው/ላት።
- በመኪና ሽያጭ፣ መኪና አስመጪና ላኪ፣ መኪና መገጣጠሚያ ወይም የመኪና ስፔር ፓርት ንግድ ፈቃድ ያለው/ላት።
-
- ተጫራቾች በሚኪናው፣ በታንከሩ ወይም መኪናውን ከነታንከሩ በአንዱ በሁለቱ ወይም በሁሉም መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ስማቸውን አድራሻቸውን እና ማህተም ማስቀመጥ አለባቸው።
- አሸናፊዎች አሸናፊነታቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ1 (አንድ) ወር ጊዜ ውስጥ በጽ/ቤታቸው ማቅረብ አለባቸው ሲሆን ከውጭ ለሚያስመጡ በውል ስምምነት የጊዜ ገደቡ ይቀመጣል።
- ተጫራቶች የጨረታ ዋጋቸውን በአሀዝና በፊደል በኢትዮጵያ ብር ብቻ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከታወቀበት ሰዓት ጀምሮ ከማህበሩ ጋር ውል መፈጸም አለባቸው።
- ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት በአየር ላይ ጸንቶ ይቆያል።
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱንና ስፔስፊኬሽን ሜክሲኮ፣ ከሳርቤት ወደ ሜክሲኮ በሚወስደው መንገድ ፌደራል ፖሊስ ዝቅ ብሎ ከሜቴክ ፊት ለፊት SNV ኢትዮጵያ ማስተባበሪያ ዋና ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ እንግዳ መቀበያ (reception) ክፍል ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 500 (አምስት መቶ) ብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000183252813 አማኑኤል ዙሪያ የወተት ልማትና ግብይት ህ/ሥ/ማህበር ገቢ ያደረጉበት ኦሪጅናል ደረሰኝ በመያዝ መግዛት ይችላሉ።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0587770494/0911708819/0924359519/0911584119 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ
ማሳሰቢያ፡-
- ጨረታው የማህበሩ የግብይት ኮሚቴ፣ ጨረታ ኮሚቴና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታንውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
