Tender Detail

Tender Details

  • Company SOUTH ETHIOPIA IRRIGATION AND LOWLAND AREA DEVELOPMENT BUREAU (የደቡብ ኢትዮጵያ መንግስት መስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ)
  • Address ጂንካ ከተማ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 251 462210071
  • Website
  • Deadline30 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Securityለሎት 1 10,000 (አሥር ሺህ ብር) እና ለሎት 2 እና ሎት 3 ለእያንዳንዱ 3,000 /ሶስት ሺህ ብር/
  • opening date2025-12-30 00:00:00
  • Categories Office Supplies And Services , Cleaning And Janitorial Equipment , Stationery Materials , Vehicle tire

የደቡብ ኢትዮጵያ መንግስት መስኖናቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ ለ2018 ዓ.ም የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን በአገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

SOUTH ETHIOPIA IRRIGATION AND LOWLAND AREA DEVELOPMENT BUREAU (የደቡብ ኢትዮጵያ መንግስት መስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ)


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የደቡብ ኢትዮጵያ መንግስት መስኖናቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ ለ2018 ዓ.ም የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን

  • ሎት 1/ የተሽከርካሪ ጎማዎች
  • ሎት 2/ አላቂ ዕቃዎች
  • ሎት 3/ ሌሎች አላቂ ዕቃዎችን በአገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ማንኛውም

  1. በዘርፋ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት የአቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው የሚገልፅ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የጨረታውን ዝርዝር ሁኔታ የሚያመለከት የጨረታ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የንግድ ፈቃዳቸውን በመያዝ ቀርበው የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ከግ/ፋ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት መግዛት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የፋይናንሻል እና ቴክኒካል ዶክመንት ፖስታ በአንድ ፖስታ በማሽግ ኦርጅናል እና ኮፒ ፖስታ በመለየት በፖስታው ላይ ማህተም በማድረግ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የሰጡት ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ ማካተት አለማካተቱን ፋይናንሻል ጨረታ ዋጋ ማቅረቢያው ላይ በግልፅ ማሳየት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 10,000 (አሥር ሺህ ብር) ብቻ። በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና ሲሆን ለሎት 2 እና ሎት 3 ለእያንዳንዱ 3,000 /ሶስት ሺህ ብር/ ብቻ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. የጨረታ ማስከበሪያ በሌላ ፖስታ አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል በሀገር ውስጥ በግዥና ንብረት ኤጀንሲ ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  8. ጨረታውን ለማደናቀፍ የሞከረ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ሆኖ ለወደፊትም በመንግስት ግዥ ጨረታ ውስጥ የማይወዳደር ስለሆነ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
  9. ማንኛውንም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፁ ማንኛውም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን አልወዳደርም ማለት አይችልም፡፡
  10. የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ማሸነፉ በፅሁፍ ከተገለፀለት በኋላ በ15 የሥራ ቀናት ውስጥ ለውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና በመያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል መፈራረም አለበት፡፡ ውሉን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀርቦ ባይገባ ባይፈጽም የጨረታ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
  11. የጨረታው አሸናፊ የሆነ ድርጅትን ወክሎ ውሉን የሚፈርም የድርጅቱ ባለቤት ሳይሆን ቀርቶ ተወካይ ከሆነ ህጋዊ ውክልና አርጅናልና የማይደመለስ ኮፒ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
  12. ለጨረታው የውል ማስከበሪያነት ያስያዘው ገንዘብ አሸናፊው ተጫራች ግዴታውን በውሉ መሰረት ካልፈጸመ በውሉ ላይ በሚገለጸው ህግ መሰረት መ/ቤቱ ተፈፃሚ የማድረግ መብት አለው
  13. ተጫራቾች የሚገዙ ዕቃዎች የሚያቀርቡት የእያንዳንዱ ዋጋ ሞልተው የሚያቀርቡና በፋይናንሻል በጨረታ ሰነዱ ላይ በሚገኘው ማቅረቢያ ፎርም መሙያ/ ዝርዝር ውስጥ ብቻ መሆን አለበት፡፡
  14. መ/ቤቱ በውሉ መሠረት ክፍያውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይፈጽማሉ፡፡
  15. ጨረታው ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከቆዩ በኋላ በ16ኛው ቀን የሥራ ቀን ከሆነ ልክ ከቀኑ 4፡00 ሣጥኑ ታሽጎ ልክ 4፡30 ተጫራቾችና ህጋዊ ወከሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
  16. ማንኛውም ተጫራች ግልጽ ያልሆነ ነገር ቢኖር በሥራ ቀንና በሥራ ሠዓት ግዥ ክፍል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  17. መ/ቤቱ የግዥውን መጠን 20% መጨመርና መቀነስ ይችላል፡፡
  18. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የደቡብ ኢትዮጵያ መንግስት መስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ

 

Save Tender