Tender Detail

Tender Details


ኢትዮ ቴሌኮም ለድርጅቱ አገልግሎት የማይሰጡ አዳዲስ እና ከአገልግሎት የተመለሱ የተለያዩ ዕቃዎችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።

Ethio Telecom (ኢትዮ ቴሌኮም)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር SC/L/WRM/002/2018

 

ኢትዮ ቴሌኮም ለድርጅቱ አገልግሎት የማይሰጡ አዳዲስ እና ከአገልግሎት የተመለሱ የተለያዩ የእጅ ሞባይሎች ቀፎዎች፤ የቤት ስልኮች እና ሞደሞች፣ የፓወር እና ኔትዎርክ ስፔር ፓርቶች፣ የፊክስድ ኔትዎርከ ዕቃዎች፣ የተለያዩ ዐይነት ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተር ሲፒዩ እና ሞኒተሮች፣ የተለያዩ ዓይነት ራኮች፣ የኔትዎርክ አንቴናዎች፣ ከአገልግሎት የተመለሱ ፕሪንተሮች፣ ፋክስ ማሽኖች፣ ሲግኒቸርፓዶች፣ ስካነሮች እና የኮምፒውተር አክሰሰሪዎች፣ ያገለገሉ ላፕቶፖች፣ ከአገልግሎት የተመለሱ የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች፣ ከአገልግሎት የተመለሱ ጀነሬተሮች፣ የተለያዩ የመኪና ስፔርፓርቶች፣ የተለያዩ ያገለገሉ ሰርቨሮች፣ የተለያዩ የአይሲቲ ስፔር ፓርቶች፣ ከአገልግሎት የተመለሱ ስክራኘ የፖል እንጨቶች፣ ብረታብረቶችንና ራኮችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከህዳር 20 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 03 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ድረስ በማንኛውም ጊዜ እና ሰዓት ከአክሽን ኢትዮጵያ ዌብ ሳይት ወይም ከኦክሽን ኢትዮጰያ መተግበሪያ በመግባት ማግኘት እና መመዝገብ የምትችሉ ሲሆን ንብረቶቹን መመልከት እንዲሁም ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የምትፈልጉ ተጫራቾች አቃቂ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና ግምጃ ቤት፣ በወሎ ሰፈር እና ቴሌ ጋራጅ በሚገኘው የኩባንያው ዕቃ ግምጃ ቤቶች እንዲሁም በምስራቅ አዲስ አበባ (ገርጂ)፣ በሰሜን አዲስ አበባ (ፈረንሳይ)፡ በምዕራብ አዲስ አበባ (አስኮ) እና በሌሎች ቦታዎች በጨረታ ዶክመንቱ በተገለጸው መሠረት በመገኘት የታደሰ መታወቂያችሁን በመያዝ መጎብኘትና መመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ኘሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction. et ላይ በመመዝገብ መወዳደር ይችላሉ።

የአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ አጠቃቀምን በተመለከተ በኦክሽን ኢትዮጵያ የጥሪ ማዕከል 9164/090511-5511 ወይም 0116-66-8828 ደውሎ መረዳት ይቻላል።

ኩባንያው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ኢትዮ ቴሌኮም

 

Save Tender