Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን የከሚሴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2018 ዓ ም ለስልጠና አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የህንጻ መሳሪያ እቃዎች፣ የግብርና እቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያ፣ ቋሚና አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች እና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እንዲሁም የሰራተኞች ደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

Kemissie Polytechnic College (የከሚሴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ)


 

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን የከሚሴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2018 ዓ ም ለስልጠና አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የህንጻ መሳሪያ እቃዎች፣ የግብርና እቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያ፣ ቋሚና አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች እና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እንዲሁም የሰራተኞች ደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፤ ስለዚህ ከዚህ በታች መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ ሲሆን

  1. የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያለው
  3. የግዡ መጠን ክብር 250,000 /ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  4. ጨረታው 15 የስራ ቀናት በአየር ላይ የሚውል ሲሆን ማለትም ከ6/4/2018 እስከ 20/4/2018 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን በ21/4/2018 ከጠዋቱ በ4:00 ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 ይከፈታል፡፡
  5. የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ 10,000 ብር /አስር ሺህ ብር/ ማስያዝ አለበት። በዋጋ መሙያ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
  6. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት አምስት የስራ ቀናት ውስጥ የጠቅላላ ዋጋ ቫት 15% ጨምሮ አስራ አምስት በመቶ የውል ማስከበሪያ ማቅረብና ውል መግባት ይኖርበታል፡፡
  7. አሸናፊው ደርጅት ያሸነፈውን እቃ ኮሌጁ ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
  8. ጨረታ የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በአል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ፋ/ን/አስ/ ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 የማይመለስ 100 ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0915549402/0913902471 ላይ በመደወል ማንኛውንም መረጃ መጠየቅ ይችላሉ

 

የከሚሴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

ከሚሴ

 

Save Tender