በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በደቡብ ወሎ ዞን የከላላ ወረዳ ፍ/ቤት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት የከላላ ወረዳ ፍ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በደቡብ ወሎ ዞን የከላላ ወረዳ ፍ/ቤት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1ኛ. የጽህፈት መሳሪያዎች፣ 2ኛ. ሌሎች የተለያዩ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ 3ኛ. የተለያዩ ሕትመቶች፣ 4ኛ. ቋሚ እቃ ወይም ፈርኒቸሮች፣ 5ኛ. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ 6ኛ. የተለያዩ ደንብ ልብስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ተጫራች በጨረታው መወዳደር ይችላል።
- በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ቲን ነምበር ያላቸው፡፡
- የግዥ መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት /ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥና የምስከርወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-2 የተጠቀሱት እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት በአየር ላይ ይቆያል፤ የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መገለጫ /ስፔሲፊኬሽን/ እና የጨረታ ሰነዱን ከለላ ወረዳ ፍ/ቤት ግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ከተ.ቁ 1 እስከ 6 የተዘረዘሩትን የጨረታ ሰነዶችን ለእያንዳዳቸው የማይመለስ 40 ብር /አርባ ብር/ ብቻ በመክፍል ከደቡብ ወሎ ዞን ከለላ ወረዳ ፍ/ቤት ግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 ማገኘት መግዛት ይቻላል።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የሎት እቃ ጠቅላላ ዋጋውን /ቫቱን ጨምሮ 1% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን አንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በጥንቃቄ አሽጎ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ድረስ በደቡብ ወሎ ዞን ከላላ ወረዳ ፍ/ቤት ግዥ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ከኅዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታኅሳስ 14 ቀን 2018 ዓ.ም በአየር ላይ ይውላል ሆኖም ታኅሳስ 15 ቀን 2018 ዓ.ም የጨረታ ሳጥኑ ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደቡብ ወሎ ዞን ከላላ ወረዳ ፍ/ቤት ግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 በዚሁ ዕለት ጨረታው በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል።
- ለበለጠ መረጃ መ/ቤቱ ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር፡- 033 451
በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት የከላላ ወረዳ ፍ/ቤት
