በአብክመ የኦሮሞ ብ/ዞን/ገንዘብ መምሪያ በኦ/ሮ ዞን ጤና መምሪያ አማካኝነት በከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ ውስጥ ለሚያስገነባው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ግንባታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል።
የአብክመ የኦሮሞ ብ/ሰብ ዞን ገንዘብ መምሪያ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2018 ዓ.ም
በአብክመ የኦሮሞ ብ/ዞን/ገንዘብ መምሪያ በኦ/ሮ ዞን ጤና መምሪያ አማካኝነት በከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ ውስጥ ለሚያስገነባው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ግንባታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል።
ስለሆነም፡-
- ተጫራቾች በግንባታ ዘርፍ BC ወይም GC ደረጃ 5 /አምስት/ እና ከዚያ በላይ ሆኖ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣የካት ተመዝጋቢ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥርና የምስክር ወረቀት እና እንዲሁም አንድ አመት ያልሞላው ወይም ታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይንም በገቢ መቀበያ ደረሰኝ በኦሮሞ ዞን ገንዘብ መምሪያ ስም በምርጫቸው በአንዱ ከዋና /Original/ የመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የሚያሳይ የጨረታ ሰነድና የተጨራቾች መመሪያ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት 30/03/18 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 21ኛው ቀን ማለትም 20/04/18 ዓ.ም ቀን 11፡30 ሰዓት ድረስ በኦሮሞ ብሄ/ዞን/ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን ዋና እና ቅጂ /Original and Copy/ ለየብቻው በታሸገ ኢንቨሎፕ ጨረታው ታትሞ ከወጣበት ቀን ከ30/03/18 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 22ኛው ቀን ማለትም እስከ 21/04/18 ዓ.ም ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በኦሮሞ ዞን ገ/ኢ/ትመምሪያ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ሠዓት በግልጽ ይከፈታል። የመክፈቻ ዕለቱ የበዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።
- የጨረታ ውጤት ለአሸናፊ ድርጂቶች በአድራሻ ለተሸናፊዎች ደግሞ በግልባጭ በደብዳቤና በመምሪያው የውስጥ ማስታወቂያ የምናሳውቅ ይሆናል።
- ተጫራቾች በሌላ ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
- መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በአብክመ የኦሮሞ ዞን ገንዘብ መምሪያ አድራሻ፣ ከሚሴ
ከአዲስ አብባ ወደ ደሴ መስመር 325 KM ላይ ከሚሴ ከተማ እንገኛለን።
ስልክ ቁጥር 033 554 0364/ 033 554 2119 ላይ በመደወል ማንኛውም መረጃ መጠየቅ ይችላሉ።
የአብክመ የኦሮሞ ብ/ዞን/ገንዘብ መምሪያ
