Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara Forest Enterprise (የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ)
  • Address ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 አዲሱ መናኸሪያ ጀርባ እንስሳት ህክምናና ላብራቶሪ ግቢ ውስጥ አማራ ደን ኢንትርፕራይዝ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 13 ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058 226 3095
  • Websitehttps://amharaforest.gov.et
  • Deadline17 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Securityበሞሉት ጠቅላላ ዋጋ 2%
  • opening date2025-12-17 00:00:00
  • Categories Furniture And Furnishing , Wood And Wood Working , Machinery , Metals And Metal Working

የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ የእንጨት መሰንጠቂያ ምላጭ (Double hard High alloy band saw Blade) ዲክሰን አንግል ሽልፍ እንዲሁም የብረት ሸልፍ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Amhara Forest Enterprise (የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ)


 

አንግል ሼልፍ እንዲሁም የብረት ሼልፍ ግዥ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር- አደኢ ግ/ጨ/---/2018

 

የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ የእንጨት መሰንጠቂያ ምላጭ (Double hard High alloy band saw Blade) ዲክሰን አንግል ሽልፍ እንዲሁም የብረት ሸልፍ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር እንዲችሉ ይጋብዛል፡፡

  1. የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤
  3. የግዥ መጠኑ ከብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) መመዝገባቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  4. በገቢዎች ባለስልጣን ዕውቅና በስሙ የታተመ ደረሰኝ ያለው፤
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በሞሉት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ለተቋሙ ገንዘብ ያዥ ገቢ በማድረግ ደረሰኙን ከሠነዱ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች ፋይናንሻል /የዋጋ መሙያ/ እና /ሲ.ፒ.ኦ/ አንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ አማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋናው መ/ቤት ቢሮ ቁጥር13 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ ቀኑ 8፡00 ድረስ መቅረብ አለበት፡፡ በዚሁ ቀን 8፡30 ላይ የጨረታ ሰነዱ ይከፈታል ቀኑ ቅዳሜ ከሆነ እስከ ቀኑ 4፡00 ድረስ መቅረብ አለበት በዚሁ ቀን 4፡30 ይከፈታል።
  8. ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አማራ ደን ኢንትርፕራይዝ ቢሮ ቁጥር 13 በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይታሸግና በዚሁ ቀን 8፡30 ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ ከሆነ 4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል 10ኛው ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ወደሚቀጥለዉ የሥራ መጀመሪያ ቀን በማዛወር ከላይ በተገለጸዉ ተመሳሳይ ሥርዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ይሁንምእንጂ ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
  9. ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ አማራ ደን ኢንትርፕራይዝ ቢሮ ቁጥር 13 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0583202985/0913488983 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  11. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) መክፈል መግዛት ይቻላል፡፡

 

የድርጅቱ አድራሻ፡- ባህር ዳር ቀበሌ 14 አዲሱ መናኸሪያ ጀርባ እንስሳት ህክምናና ላብራቶሪ ግቢ ውስጥ አማራ ደን ኢንትርፕራይዝ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 13 ባህር ዳር

ማሳሰቢያ፡- ከላይ የተዘረዘሩት የእንጨት መሰንጠቂያ ምላጭ (Double hard High alloy band saw Blade) ዲክሰን አንግል ሸልፍ እንዲሁም የብረት ሸልፍ ብዛትና ዝርዝር መገለጫው ከጨረታ ሰነዱ የዋጋ መሙያ ሰንጠረዥ ላይ የተገለፀ መሆኑን የሚቀርበውም በዚሁ ዝርዝር መግለጫ መሰረት መሆኑን እናሳስባለን።

 

የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ

 

Save Tender

የWindows of Hope 2026 ፕሮጀክት ያሰባሰባቸው አስር አጋር ድርጅቶች ለቆዳ እና የልብስ ስፌት ስራ ማሽኖች አቅርቦት ብቁ የሆኑ አቅራቢዎችን በድጋሚ...

READ MORE
Procurement of Machinery

READ MORE
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን 6ኛ እስከ 8ኛ ፎቅ ያሉትን ቢሮዎች መጋረጃ ከዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰ...

READ MORE