በቂርቆስ ክፍለ ከተማ መሬት ልማት አስተዳደር ጽ/ቤት የግዥ ቡድን ለተለያዩ የስራ ክፍሎች የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቂርቆስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ መሬት ልማት አስተዳደር ጽ/ቤት የግዥ ቡድን ለተለያዩ የስራ ክፍሎች የሚውል:-
- ሎት.1 ደንብ ልብስ
- ሎት.2 አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች
- ሎት.3 አላቂ የጽዳት እቃዎች
- ሎት.4 ልዩ ልዩ እቃዎች
- ሎት.5 የመኪና ኪራይ አገልግሎት
- ሎት.6 የኮምፒውተር ተዛማጅ እቃዎች
- ሎት.7 የህትመት ስራዎች
- ሎት.8 የጫኝና አዉራጅ ስራዎች
- ሎት.9 ዲጄ፣ዲኮርና ሳውንድ ሲስተም
- ሎት.10 የመሬት ባንክ ታፔላ ስራዎች
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑ ግብር የከፈሉ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበበትን ቲን ማቅረብ የሚችል እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቅራቢ ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ።
- የጨረታ ሰነዱን ሁሉም ሎት በአንድ ላይ የማይመለስ 300 /ሶስት መቶ ብር /ብቻ በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ከ2፡30 እስከ 11፡30 በመሬት ልማት አስተዳደር ጽ/ቤት በግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 1-02 መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ሎት 1 የደንብ ልብስ ብር 2,000፣ ሎት 2 አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች ብር 5,000፣ ሎት 3 አላቂ የጽዳት እቃዎች ብር 2,000፣ ሎት 4 ልዩ ልዩ እቃዎች ብር 3,000፣ ሎት 5 የመኪና ውስጥ እቃዎች ብር 5,000፣ ሎት 6 የኮምፒውተር ተዛማጅ እቃዎች ብር 20,000፣ ሎት 7 የህትመት ስራዎች ብር 3,000፣ ሎት 8. የጫኝና አዉራጅ ስራዎች ብር 2,000፣ ሎት 9 ዲጄ፣ዲኮርና ሳዉንድ ሲስተም ብር 3,000፣ ሎት 10. የመሬት ባንክ ታፔላ ስራዎች ብር 10,000 በባንከ በተመሰከረለት c.p.o /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛ ቀን ድረስ በቢሮ ቁጥር 1-02 አንደኛ ፎቅ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት እቃዎች ናሙና ጨረታ ከመከፈቱ በፊት መቅረብ አለበት፡፡ የሎት 10 የመሬት ባንክ ታፔላ ናሙና በእንጨት ወይም በብረት ማቅረብ አለበት
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ተዘግቶ ተጫራቾች ባሉበት ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት በመሬት ልማት አስተዳደር ጽ/ቤት በሚገኘው አዳራሽ የሚከፈት ሲሆን የበዓል ቀን ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
- ለጨረታ ከቀረቡት እቃዎች ዝርዝር ውስጥ ጽ/ቤቱ እስከ 20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለጨረታ የሚቀርቡ እቃዎች ጥራታቸውን የጠበቁ መሆን አለባቸው
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት
ስልክ ቁጥር:- 0115580040 ወይም 011-854-57-12/0913146587 መደወል ይችላሉ
አድራሻ:- ከእስጢፋኖስ ወደ 22 በሚወስደው መንገድ ኖክ ማደያ አጠገብ በሚገኘው ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፑል አስተባባሪ ጽ/ቤት የግዢ ቡድን ቢሮ ቁጥር 1-02 1ፎቅ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቂርቆስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
